ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚንየም የተፈጠረው ምንድነው ?ኢትዮ ኤፍኤም 107.8 ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ያገኘው ይሄን ይመስላል፡፡በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ…

ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚንየም የተፈጠረው ምንድነው ?

ኢትዮ ኤፍኤም 107.8 ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ያገኘው ይሄን ይመስላል፡፡

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ ኮምዶሚኒየም በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመው የግድያ ወንጀል፤ የተፈፀመው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ነው፡፡

በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በምትሰራ ወንጀል ፈፃሚ አማካኝነት ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሶስት አመት ህፃናት ህይወት አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት ወንጀል ፈፃሚው በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡

የህፃናቱ ህይወት በወንጀል ፈፃሚዋ እንዴት እንዳለፈና ሌሎችንም መረጃዎች ፓሊስ ተጨማሪ መረጃ እያጣራ እንደሚገኝ እና ህብረሰተቡም እንዲረጋጋም ም/ ኮማንደር ማርቆስ አደራ ብለዋል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

Source: Link to the Post

Leave a Reply