You are currently viewing ቦሌ አየር ማረፊያ ላይ ታፍና የተወሰደችው አክቲቪስት፣ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ታስራ እንደምትገኝ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ግንቦት 14…

ቦሌ አየር ማረፊያ ላይ ታፍና የተወሰደችው አክቲቪስት፣ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ታስራ እንደምትገኝ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 14…

ቦሌ አየር ማረፊያ ላይ ታፍና የተወሰደችው አክቲቪስት፣ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ታስራ እንደምትገኝ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው ቦሌ አየር ማረፊያ ላይ ታፍና የተወሰደችው የአክቲቪስት፣ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ ባለቤት አቶ ፍጹም ገ/ሚካኤል እንደገለጹት የባለቤታቸውን አድራሻ ሰው በሰው ለማወቅ ችያለሁ ብለዋል። በዚህም አሁን ላይ በሶስተኛ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ታስራ ትገኛለች፤ ሄጀም ጠይቄያታለሁ ብለዋል አቶ ፍጹም። በአካሏ ላይ ምን የደረሰ ጉዳት የለም፤ እስካሁን የተጠየቀችውም ነገር የለም ብለዋል። አቶ ፍጹም “የ7 ወር ህጻን ልጅ ጥላ የታፈነችውን ባለቤቴን አድራሻ ንገሩኝ” ሲሉ ጥሪ ማፍረጋቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ እለት ግንቦት 13/2014 የታፈነው ድምጻዊ ዳኜ ዋለም ተፈቷል። “አለሁ ደህና ነኝ፤ የተጨነቃችሁልኝ እግዚ አብሄር ያክብርልኝ፤ ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ።” ሲል መልዕክቱን አረጋግቷል። በተያያዘም በአዲስ አበባ የባልደራሱ ናትናኤል አቤል ግንቦት 13/2014 መታሰሩን የገለጸው ፓርቲው በጣም በርካታ የባልደራስ አባላት ደግሞ እየታደኑ ነው ብሏል። ግንቦት 14/2014 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በዋሽንግተን በጅምላ እስሩና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ አቶ እስክንድር ነጋ ሀገራዊ ጥሪ የሚያስተላልፉበት ህዝባዊ ስብሰባ ይደረጋል ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply