ቦሪስ ጆንሰንና ሪሺ ሱናክ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስተር ለመሆን ብርቱ ፉክክር እያደረጉ ነዉ ተባለ፡፡የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ሊዝ ትረስ ከስልጣን ለመዉረድ መወሰናቸዉን ተከትሎ ቦሪስ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Bzx1uU9tZvl3Sh3ASiPP7q7mqubJJoQOiK9JKUShD-arUEBPbJvTh_3Ed8OM6T6cOxzY1rn-5DK3M9snGwHVw6Re7uPdrpLRwpBmFXM5Hbv5KcxsxJD-FHMTUjjuwhBaSomBFAljmyaPCZcTsUiWDF89ocw7qfWySjEUtOX_VeqSZJ7EfcHNQyKh3We43nyemMFkTooPycEX74Cw4lx8c_8egoG_mMm9Q-Yz_C3-28yGXn9YjbhgSQtnvWz7dm7rjFxtYg4rhUv5lqPFQbQDea1VTM7Y9WRtNP7jL-6vVaW7j1d4TQgz5jJ1TsxbyBa1QPSf7T64jIFDjoBkx8ibvQ.jpg

ቦሪስ ጆንሰንና ሪሺ ሱናክ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስተር ለመሆን ብርቱ ፉክክር እያደረጉ ነዉ ተባለ፡፡

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ሊዝ ትረስ ከስልጣን ለመዉረድ መወሰናቸዉን ተከትሎ ቦሪስ ጆንሰንና ሪሺ ሱናክ ለጠቅላይ ሚኒትረነት ቦታዉ ትልቅ ግምት አግኝተዋል፡፡

ሁለቱ ተፎካካሪዎች የወግ አጥባቂ ፓርቲ ድምፅ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት መጀመራቸዉ ተሰምቷል፡፡
ምርጫዉን አሸንፎ ሊዝ ትረሰን የሚተካዉ ሰዉ በቀጣይ ሳምንት በይፋ ይታወቃል፡፡

ከ45 ቀናት በፊት ከስልጣን የወረዱት ቦሪስ ጆንሰን ምርጫዉን የሚያሸንፉ ከሆነ ድጋሜ እንግሊዝን የመምራት እድል ያገኛሉ፡፡

ሪሺ ሱናክ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡
በሀገረ እንግሊዝ አሁን የሚደረገዉ ምርጫ በስድስት አመታት ዉስጥ ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply