ቦርንመዝ ስኮት ፓርከርን አሰናበተ፡፡ አዲሱ የውድድር ዘመን ከተጀመረ የተከናወኑት አራት ጨዋታዎች ብቻ ናቸው፡፡ ቦርንመዝ ግን ቅዳሜ ለት ቡድኑ በሊቨርፑል 9-0 የተሸነፈበትን መንገድ ገምግሞ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/rSK6AeQZH0sVMRre-SjYCz6BO-_jN9OTH8nyk9AZtwQeVPMl0PnkH3dh2SEJM2n_rSp43Y3N33kyYrYOfCZjDpcLmt9TGtT_PA0f-s8tu7x9NieQljkYVKWUlATVYasXcue5zQcTwh28GuaQsf-YLWxNzeox9WhWdGBDzoNyfpv7SpG5olSMkdKqNFX7RyIG1KBR3UB_Z2slV0eGpRsxzyaaRdnRxxVYj4J9wWkBQVWPX5kfodSREK8YXUz5FqKrZbIKJkT4x7G84GltIOYGuqC44tXm34rdnD_9cRYAmv_SQvEEuy5TjmjdcEpwlY2K1InnB1MCqM-biekQdCw6Bg.jpg

ቦርንመዝ ስኮት ፓርከርን አሰናበተ፡፡

አዲሱ የውድድር ዘመን ከተጀመረ የተከናወኑት አራት ጨዋታዎች ብቻ ናቸው፡፡

ቦርንመዝ ግን ቅዳሜ ለት ቡድኑ በሊቨርፑል 9-0 የተሸነፈበትን መንገድ ገምግሞ ስኮት ፓርከርን ለማሰናበት ወስኗል፡፡

የ41 ዓመቱ ፓርከር ከሽንፈቱ በኋላ ቡድኑ በፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ለመሆን በቂ ድጋፍ እንዳልተደረገለት ጠቅሶ በውጤቱ አለመገረሙን ተናግሯል፡፡

የፕሪምየር ሊጉን የመጀመሪያ ጨዋታ ቢያሸንፍም ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ተረትቷል፡፡

‹‹ እንደ ቡድን እና ክለብ መሻሻላችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡

ክለቡ ባስቀመጠው ስትራቴጂ መሰረት ዘላቂነት ያለው ዕድገት ማሳየት ይኖርብናል ›› በማለት የክለቡ ባለቤት ማክሲም ዴሚን ተናግረዋል፡፡

በአቤል ጀቤሳ

ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply