ቦርዱ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት ያላሟሉ ሁለት ተጨማሪ ፓርቲዎችን ሰረዘ

ቦርዱ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት ያላሟሉ ሁለት ተጨማሪ ፓርቲዎችን ሰረዘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሰረት ማሟላት ካለባቸው መስፈርቶች እንዲያሟሉ ከተጠየቁት መካከል  አራት ፓርቲዎች መስፈርቱን ያሟሉ ሲሆን ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ባለማሟላታቸው መሰረዛቸውን አስታወቀ።

መስፈርት  በማሟላት ያጠናቀቁ

  1. የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/- 39 በመቶ
  2. የአፋር ሕዝብ ፓርቲ /አሕፓ/- 45 በመቶ
  3. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ጋዴፓ/ -94 በመቶ
  4. የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ /አነግፓ/ – 48 በመቶ

ባለማሟላታቸው  የተሰረዙ

1.የመላው ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /መኦሕዴፓ/ የመስራች ፊርማ ናሙና ማረጋገጫ ከ35 በመቶ በታች በመሆኑ እና የ1 ሺህ 142 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ፣

 

2.የሲዳማ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሲብዴፓ/ – 778 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ እና በምስክርም መረጋገጡ የቀረበ ነገር ባለመኖሩ እንደተሰረዘ ተጠቁሟል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

The post ቦርዱ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት ያላሟሉ ሁለት ተጨማሪ ፓርቲዎችን ሰረዘ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply