ቦርዱ ኮቪድ19 በምርጫው ሂደት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ እና የመከላከያ መንገዶች ላይ እየመከረ ነው

ቦርዱ ኮቪድ19 በምርጫው ሂደት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ እና የመከላከያ መንገዶች ላይ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮቪድ19 በምርጫው ሂደት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ እና የመከላከያ መንገዶች ላይ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ነው፡፡

ፓርቲዎቹ በመጭው ሃገራዊ ምርጫ ዙሪያ ማማከር፣ በምርጫው ያላቸውን ግብዓትና አስተያየታቸውን መቀበልም የምክክሩ አካል ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ኮቪድ19 በምርጫ ትግበራ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ፣ አሰራር እና የመመሪያ አቅጣጫዎች ማስቀመጥ ላይም ያተኮረ ነው፡፡

በውይይቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጭው ሃገር አቀፍ ምርጫ ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት አቅርበዋል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳተፉበት ውይይት የምርጫ ፀጥታ እና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዝግጅት ለፓርቲዎቹ ቀርቧል።

ቦርዱ የምርጫ ዋና ዋና ተግባራ እና የሚከናወንበትን ጊዜ በተመለከተም ገለጻ አድርጓል።

በለይኩን ዓለም

The post ቦርዱ ኮቪድ19 በምርጫው ሂደት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ እና የመከላከያ መንገዶች ላይ እየመከረ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply