ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ሳማንታ ፓወርን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅትን እንዲመሩ ሹመት ሰጡ።በቀድሞው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን መንግስታቱ ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር…

https://cdn4.telesco.pe/file/XKefGVC2ttpwpw3_6H08dlKippPhJ8IzYCengUYjpwrp51WvL5nzZdBWrhHafWTyKJ9Oxw9XShs22IWb6HnvaZiTWzNVBWoAzi3TMCChITtFmHlDbQgR4m69dYdFNihxn8EP4nJ8Y0LhGseao1p2-x_hEjLI41oszOqXV2SFXVhpcrA907lr3mxhybTmo3IOWlLGB75czrxiP4VlIBQ8yvl-QdF34fPYpv8xS3N7ne-1SVJFaIt45puzHQXp4r1qc1FXUsq0u1A-OIwFPgB89DJMyqr6T-v5jW4X2az-5HBCbnnjG481HGxYMFGK6dMUMP4w-VZtykO02xg3Bk_PpA.jpg

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ሳማንታ ፓወርን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅትን እንዲመሩ ሹመት ሰጡ።

በቀድሞው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን መንግስታቱ ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ሳማንታ ፓወር አዲስ ሹመት አግኝተዋል።

ሳማንታ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID)n እንዲመሩ በባይደን ተሹመዋል፡፡

ባይደን ከሳማንታ ፓወር በተጨማሪም ኩርት ካምቤልን የነጩ ቤት ቤተመንግስት አስተባባሪ አድርገው መምረጣቸውን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡

በባይደን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ሀላፊ ሆነው የተመረጡት ሳማንታ ፓወር በኦባማ አስተዳደር የብሄራዊ ደህንነት ካውንስል ሆነውም ለአምስት አመታት ያህል አግልግለዋል፡፡

በተጨማሪም የሰብአዊ ምብት እና የውጭ ጉዳይ አማካሪ በመሆንም አገልግለዋል።

ሳማንታ ፓወር የኦባማ አስተዳደር በሶርያ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆምና አሜሪካ እጇን እንዳታሰገባ በከፍተኛ ሁኔታ ሲታገሉ የነበሩ የፖለቲካ ሰው ናቸው፡፡

በወቅቱ በገዛ ፍቃዳቸው ነበር ከብሄራዊ ደህንነት አማካሪነት ስራቸው ለመልቀቅ የወሰኑት፡፡

ያን ተከትሎ ነበር ሳማንታ ፓወር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳዶር በመሆን የተመረጡት፡፡

የ50 አመቷ ጋዜጠኛ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ሳማንታ ፓወር የፑሊትዘር ሽልማት ካገኙ ስመጥር ጋዜጠኞች መካከል ስሟ ይጠቀሳል፡፡

ሳማንታ ፓወር የፑሊትዘር ሽልማት እንድታሸንፍ የረዳት በፈረንጆቹ 1990 በቦስኒያ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ለንባብ ካበቃችው መጽሀፍ ጋር በተያያዘ ነበር፡፡

ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ አሜሪካንን በፕሬዘዳንትነት መምራት የሚጀምሩት ጆ ባይደን ባሳለፍነው ሳምንት ትውልደ ኢትዮጵያዊውን ዮሀንስ አበርሃምን የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሃላፊ አድርገው መሾማቸው ይታወሳል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

Source: Link to the Post

Leave a Reply