ተመድ በሰሜን ኢትዮጵያ በድርቅ ሳቢያ የተከሰተውን እና የከፋ የረሃብ ሁኔታን ለማስታገስ 17 ሚሊየን ዶላር መመደብ ታዉቋል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ሰጭዎች ትናንት እን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/FmoTVG1vlP1-9oOZKneRzO2ZApMEKepldh-gttX_kTAqrD1YZgz1A5HNAuPov9DGoLcZAvLK6-AH8lcNke1Qx3IfQ3OYaxBMv-8rxA0nByOFl5m91wuaRU31hdhoo9x0iX6GYhDP4Dj_JjTPJvT7N4C9klpeHWpPqDlZZUyPTfHIzTEY0_YR2ZjM0_9p-rLXtNb72xfO5upjzi8OuLvWAOnS9B96N0R7NPr2X-wMdI2E3pO3my2VNDz4YfbPmH8GdDpA4vmzAWjNY3qHJikoIq-9f5UeO4K7HEvudF2DsGTeaeO9dGJcqGyKyKRzqVduRv_eXnB8baA2gOGrg-i0-w.jpg

ተመድ በሰሜን ኢትዮጵያ በድርቅ ሳቢያ የተከሰተውን እና የከፋ የረሃብ ሁኔታን ለማስታገስ 17 ሚሊየን ዶላር መመደብ ታዉቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ሰጭዎች ትናንት እንዳስታወቁት በሰሜን ኢትዮጵያ በድርቅ ሳቢያ የተከሰተውን እና የከፋ የረሃብ ሁኔታን ለማስታገስ 17 ሚሊየን ዶላር ለቀዋል።

የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ አማካኝነት ከማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ፈንድ  የተለቀቀው ይህ ገንዘብ በኤልኒኖ ምክንያት የተከሰተው አዲስ ድርቅ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ መሆኑ ነዉ ተብሏል።

“አዲሱ ድርቅ እየተባባሰ በመምጣቱ ከሐምሌ እስከ መስከረም ባለው የዝናብ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኦቻ አስታዉቋል ።

የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply