ተመድ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ከ35 ሚሊየን ዶላር በላይ መልቀቁን ገለፀ

ተመድ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ከ35 ሚሊየን ዶላር በላይ መልቀቁን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ህግን በማስከበር እርምጃው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 35 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ መልቀቁን አስታወቀ።

ድጋፉ ለዜጎች የውሃ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና የህክምና ቁሳቁሶችን ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።

የተመድ ድንገተኛ አደጋዎች ፈንድ በኢትዮጵያ የጤና ተቋማት የታመሙ እና የቆሰሉ ሰዎችን መከባበከብ እንዲችሉ መድሃኒት፣ ጓንት እና ሌሎች አቅርቦቶችን እንደሚያቀርብ ነው የተነገረው።

እንዲሁም በሱዳን ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች መጠለያ፣ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ እና የጤና እንክብካቤ ለማድረግ ድጋፉ በተመድ ድንገተኛ ፈንድ በኩል ጥቅም ላይ እንደሚውል ተጠቁሟል።

የተመድ ማዕከላዊ የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ፈንድ በኢትዮጵያ ውስጥ ድጋፍ ለሚደረግላቸው 13 ሚሊየን ዶላር እና በሱዳን የስደተኞች ጣቢያ አዲስ ለሚገቡት 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ መልቀቁን ነው ያስታወቀው።

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የሚገኘው የተመድ የሰብዓዊ ፈንድ በቀጣይ 12 ሚሊየን ዶላር እና በሱዳን የተመድ የሰብዓዊ ፈንድ 5 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚለቁ ይጠበቃል።

ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን እና ህፃናት በድጋፉ ቅድሚያ የሚሰጣቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ተመድ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ከ35 ሚሊየን ዶላር በላይ መልቀቁን ገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply