ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13 እንዲያስተካክሉ ጥሪ ቀረበየመንግስት ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13 እንዲያስተ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/IGOmyj_30GnoEhTxTGbx7iA7axkoi1JYsbCtJ6iR9usfPch6y_UYODeDEpCh_xvFBSnQroXyxUqaXs8aH89g1K0L587p98dGGXuDOhu03J9kmhLpl3lMJfW9lFK8Nrp1gxjiMCIA_cdwCX_9_Ydz7x-Cx4T775kK9LyMN3UiyOJTy4dBb4nNVqa6OxvdRy10kUfpqwrXsTkxM8RBX68dlY170eJYCFXiKnXi5Prwbi9EwAk2YtdW_rQbyFa6MRLhiTZzit7SRq72Zeka3xSJue5QCO_niMjZbMtxhCCeOYGyKgqFJoWHBJqUYKiO88n7Bxi7Sv1qT8ADB5wgpMzNFQ.jpg

ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13 እንዲያስተካክሉ ጥሪ ቀረበ

የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13 እንዲያስተካክሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸውን የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን በመግለፅ የሚከተሉትን መረጃዎች ተማሪዎች እንደሚለከቱ ጠይቋል፡፡

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply