ተረኝነት አለ ወይ?  (ታህሳስ 22፣ 2013ዓ.ም) ኢህአዴግ በመከላከያው 80 % .የሀገሪቱን ድርሻ ይዞ ነበር፡፡ የኢህአዴግ ገዥ መንፈስም ህወኃት ነበር፡፡ ህወኃት  የጠቅላይ አዛዥነቱን…

ተረኝነት አለ ወይ? (ታህሳስ 22፣ 2013ዓ.ም) ኢህአዴግ በመከላከያው 80 % .የሀገሪቱን ድርሻ ይዞ ነበር፡፡ የኢህአዴግ ገዥ መንፈስም ህወኃት ነበር፡፡ ህወኃት የጠቅላይ አዛዥነቱን…

ተረኝነት አለ ወይ? (ታህሳስ 22፣ 2013ዓ.ም) ኢህአዴግ በመከላከያው 80 % .የሀገሪቱን ድርሻ ይዞ ነበር፡፡ የኢህአዴግ ገዥ መንፈስም ህወኃት ነበር፡፡ ህወኃት የጠቅላይ አዛዥነቱን በኢህአዴግ ስም ይዞ ነበር፡፡ ብልፅግናስ? ብልፅግናንን እስካሁን ከተግባሩ አንፃር በትክክል የገለፀው ምርጥ ፖለቲከኛ ሽመልስ አብዲሳ ናቸው፡፡ በሽመልስ ብልፅግና መሰረት ፖለቲካ ቁማር ሲሆን ማጭበርበር የፖለቲካ ብስለት ነው፡፡ ህዝብ የሚፈልገውን ተናግሮ የሚፈልጉትን መስራት ፖለቲካዊ አሸናፊነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሞኙን አሳምነን፣ ብልሁን አደናግረን እንገዛለንም ብለዋል፡፡ በጣም ብልሆችን ደግሞ እናስራለን ብለዋል፡፡ በዚህ መሰረትም አዲስ አበባን ለመዋጥ ባልደራስን እና አመራሮችን ለማጥፋት ተሰርቷል፡፡ አዲስ አበባ እንዳትዋጥ አይቆረጤሜ ያደረጋት እስክንድር ነጋ ታሰረ፡፡ እንደ ሽመልስ ያንድ ወቅት ሚስጢራዊ ንግግር ብልፅግና የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈልገው ለኦሮሞ የበላይነት ብቻ ነው፡፡ የጠቅላይሚኒስትሩ የውጭ ግንኙነት እና የፖለቲካ ጉዳዮች አማካሪ ሌንጮ ባቲ ቀጣዮቹ 3 ሺ ዘመናት በብልፅግና አማካኝነት የኦሮሞ ገዥነት ይረጋገጣል ብለዋል፡፡ ይህ እንዲሳካ ደቡብ ክልልን ለመዋጥ እነ አባዱላ በታተኑት ፡፡ ሀረርን አፈራረሷት፡፡ አማራን በጎጥ ለመከፋፈል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ አባዱላ እንደ አቦይ ስብሃት አባዱላ የደርግ ወታደር ናቸው፡፡ በህወኃት ተማርከው ኢህዴን ሆኑ፡፡ ከኢህዴን ኦህዴድ ሆነዋል፡፡ ዛሬ ብልፅግና ሆነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሆነዋል፡፡ አባዱላ ደቡብን ለመዋጥ አፈራርሰዋል፡፡ እነ ጊዲዮ ፣ኮንሶ፣ ከፊል የጋም አካባቢን ለመዋጥ የተግባር እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡ ቅርስ እያወደሙ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ካላት 300 ሺ ሰራዊት 50 ሺው ከትግራይ፣ 40 ሺው ከወላይታ አካባቢ ነበር፡፡ አሁን ይህ ሁሉ ሰራዊት ከመከላከያው የለም፡፡ እነ አባዱላ ይሄን ሰራዊት በኦሮሞ ለመሙላት በህወኃት መውደቅ ሰበብ እየጣሩ ነው፡፡ እስካሁን ከኦሮሞ አራት ጀኔራሎች ባጫ ደበሌን እና አለምሸች ድጋፌን ጨምሮ ሲመረጥ፣ ከአማራ ጀኔራል አበባው ታደሰ ብቻ ተመልሷል፡፡ ተራ ወታደሩን ሁሉ በኦሮሞ ለመሙላት በዕቅድ እየሰሩ ነው፡፡ መከላከያው ለእነ አባዱላ ታዛዥ ከሆነ በኃላ የክልል ልዮ ሀይል ሙሉ በሙሉ ይጠፋል፡፡ የሰላም ሚኒስትሯ እና የእነ አባዱላ ታዛዥ የሆኑት ሙፈሪያት ከሚል ልዮ ሀይል ህገመንግስታዊ አይደለም ያሉት በዋዛ አልነበረም፡፡ አንደኛው መከላከያ በምንፈልገው መንገድ እንሰራዋለን ብለው በማሰብ ሲሆን፣ ሁለተኛው የአማራ ልዮ ሀይል ዝና ከፍ ሲል ደንግጠው ትኩረት ለመንፈግ ነበር፡፡ ስለዚህ መካላከያው እንደ ህወኃት በአንድ ዘውግ ከገባ ልዮ ሀይል ይፈርስና ብልፅግና የአባዱላ ብቻ ይሆናል፡፡ በነገራችን ላይ አባዱላ የህወኃቱ ስብኃት ነጋን ተክተው እየሰሩ ሲሆን፣ ግሩማ ብሩ ደግሞ አባይ ፀሃየን ወክለው ኢኮኖሚውን ይመሩታል፡፡ የፍትህ ተቋሙ ሙሉ በሙሉ በእነ አባዱላ የተያዘ ሲሆን፣ በቀጥታ ለአባዱላ እና ለግርማ ብሩ በመታዘዝ የማይፈልጉትን ባለሀብት ለማጥፋት እየሰሩበት ነው፡፡ በበርካታ የግል ባንኮች ላይም ምርመራ ጀምረዋል፡፡ ሀብቱን በሙሉ በእነ አባዱላ ስር ለማድረግ ሌላውን ባለሀብት ለማጥፋት እነ ግርማ ብሩ እየሰሩ ነው፡፡ ከመከላከያው አንፃር መጀመሪያ የህወሓት የበላይነት ይታይበት ስለነበር አብይ አህመድ የራሱን ሪፐፒሊካን ጋርድ መስርተዋል ፡፡ ይህ ሪፐፒሊክ የእነ አባዱላ እዝ ነው፡፡ ሪፐፒሊካኑን የሚያግዝ የኦሮሚያ ልዮ ሃይል ወደ 500 ሺ ደርሷል፡፡ የመከላከያ አዛዦች በሙሉ የአባዱላ ምልምሎች ሆነዋል፡፡ አብይ አህመድ የስልጣን ጥማታቸው ከብሄርተኝነታቸው ቢበልጥባቸውም፣ የእነ አባዱላ ተላላኪ ከመሆን ግን አላመለጡም ፡፡ አዲስ አበባ እንዲዘረፍ እና ህገወጥነት እንዲበረክት በማድረግ በኩል ለታከለ ኡማ ድጋፍ ሰጭው አብይ አህመድ ናቸው፡፡ ታከለ የጀመረውን አዳነች እንድትጨርሰው ትዕዛዝ ሰጭም አብይ አህመድ ናቸው፡፡ አብይ አህመድ የሚያምናቸው አማካሪዎቹ ሌንጮ ባቲ ፣ ግርማ ብሩ እና አባዱላ ናቸው፡፡ ቤተመንግስት ሲገቡ ከጨፊው ምክርቤት የተገባ እንጂ ከኢትዮጵያ ቤተመንግስት የተገባ እንደማይመስል ቤተመንግስቱን የረገጡ ሁሉ ይናገሩታል፡፡ እነ ብርሃነመስቀል፣ሀይሉ ጎንፋን አምባሳደር አድርገው የሾሙት አብይ ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ሲጠቃለል ብልፅግና የኦሮሞ ብልጽግና ክንፍ ነው፡፡ የአማራው ብልፅግና ከብአዴን በባሰ የበሰበሰ እና በፖለቲካ ድንቁርና በሚማቅቀ ሰዎች ተሞልቷል፡፡ ብዙዎቹ አይገባቸውም፡፡ ቢገባቸው አይደፍሩም፡፡ ቢደፍሩም ህብረት የላቸውም፡፡ ህብረት እንዳይኖራቸው አብይ አህመድ በሰላዮቹ አማካኝነት ይከፋፍሏቸዋል፡፡ የአማራ መከፋፈል ለእነ አባዱላ የበላይነት ምቹ ሜዳ ሆኗል፡፡ የአማራ ብልፅግናዎች ዛሬ እና ነገን ረስተው ሁሌም ስለህወኃት እንዲያወሩ ይበረታታሉ፡፡ ሌላ ነገር እንዳይፅፉማ ታግደዋል፡፡ ብዙዎቹ የአማራ ብልፅግና የሚፅፉትንም ሆነ የሚናገሩትን አይኖሩትም፡፡ ነገር ግን ብዙው መንጋ ስለሆነ አንደበታቸውን እያመነ በተስፋ ይኖራል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አደገኛ መንገድ እየተጓዘች ነው፡፡ ወደ አደገኛ መንገድ የሚነዳት ደግሞ የእነ አባዱላ ሀይል ነው ፡፡ ዛሬ ላይ አባዱላም፣አባይ ፅሃየም ፣ ህወኃትም ቤተመንግስት ናቸው፡፡ የሞተውን ህወኃት እየተቹ ያለውን ህወኃት አለመሞገት ፖለቲካዊ አድርባይነት ነው፡፡ ህዝቡ አንደበትን ከማመን ተግባርን መዝኖ ካልታገለ ቀጣይም ብዙ መፈናቀል አለ፡፡ብዙ ሞት አለ፡፡ ላለመሞት ሁኔታውን በአግባቡ ገምግሞ ኢትዮጵያን የጋራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply