ተስፋዬ መንግስቱ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

ማክሰኞ መስከረም 3 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ተስፋዬ መንግስቱ ፈቄ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።

ተስፋዬ ከዚህ በፊት የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ሆነው የሰሩ ሲሆን፤ ሹመታቸው ሲሰጥ ያላቸው የትምህርት ዝግጅት፣ ህዝባዊ ተቀባይነትና የሥራ ታታሪነታቸውን ከግምት ያስገባ መሆኑ ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ከንቲባ የነበሩት ውብሸት አያሌው ባሳለፍነው ነሐሴ 26 ቀን 2014 ምሽት ላይ ከሥራ ወጥተው ወደ ቤታቸው በመግባት ላይ ሳሉ፤ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply