ተቆፍረው ክፍት በተተው ጉርጓዶች ውስጥ ለመዋኘት ሲሞክሩ የሶስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ተቆፍረው ክ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/ImXqdavRd90TSLHDJBoMRL-b_IEdyJ3AZAv4l42gv0aWJZXN4Ign3DxrIDgeTuzxTmC5T35ZaiWne8FVj6SRmiRKpL9ngUyYvsLnh_mwPynZCRwgTYPgAeOyAeQGMJ5JjeNhaaFUQFy_LISomfgfpdWOLX9vqBS_eoz_2EO0Weq5otU4sRXRjGfZU7bzoUhjlU7k8dzn-00H4esUYktN55xqqKWPKUTdp2qY6kBqBhyAETZe4wrqBWesHbUqLpkIDmLA7uzUrnzU0IvO_igjvyclZDAaJrM1qdPSVCA1NWGQKfKighJAzcLhOlV6pPmP-AIsUfwlEKawDKkm8ORLBg.jpg

ተቆፍረው ክፍት በተተው ጉርጓዶች ውስጥ ለመዋኘት ሲሞክሩ የሶስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ተቆፍረው ክፍት በተተው ጉርጓዶች ውስጥ ገብተው ለመዋኘት ሲሞክሩ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ብቻ በተለይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ተቆፍረው ክፍቱን በተተው ጉርጓዶች ውስጥ ዋና ለመዋኘት የገቡ የ3 ሰዎች ህይወት ሊያልፍ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ድንጋይ እና ማእድናት ለማውጣት በሚል የሚቆፋፈሩ ጉርጓዶች ክፍት በመተዋቸው ምክንያት ውሃ እንዲያቁሩ እና ዋና ለመዋኘት የሚገቡ ሰዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸው፤ የ15፣18 እና የ19 አመት ታዳጊ እና ወጣቶች ክፍቱን በተተው ጉርጓዶች ውስጥ ዋና ለመዋኘት ገብተው ህይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በአዲስ አበባና አካባቢው ክፍቱን በተተው ጉርጓዶች ዋና ለመዋኘት በሚል ታዳጊዎች እና ወጣቶች ለህልፈት እተዳረጉ ሲሆን ታዳጊዎች እና ወጣቶች ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ ወላጆችም የቅርብ ክትትል ሊድርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
ህዳር 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply