ተቆፍሮ ክፍቱን የተተወ ጉድጓድ የሰው ህይወት ቀጠፈ፡፡ዛሬ ሀሙስ መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታዉ ቡልቡላ ቦሎ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ተቆፍሮ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/YdnIAL5wAYOn8z96WpjZCEjUROGGyX0UIk8Tr8WD1IzrskuYyYxyJhD6vR_jF-6qX_RbMOUc32kDl98A6yVpK_SJ7m77lJqAmlgZCX16AoM9V5aO265-lmVkee8-KYBtIbbLN4I9pbYd7Iotp9l3rWQr7T2PdVAgLKj-zZH22OlYmnVvXMfT6Tz3VkTwhynexIjLyt4cdXfyHGDGS6fhyAGYmRc2AjBJIazNOBstuuPaQzMcMKLdOdk2KogblfBCQMf6ezOXYfRK8hsTbk_A0AAaLMVAFWxjEIm_PpElbpejh9Gsuh2K-o5xvBceGO5ucldnoTrVtx-eg7r6G52hQg.jpg

ተቆፍሮ ክፍቱን የተተወ ጉድጓድ የሰው ህይወት ቀጠፈ፡፡

ዛሬ ሀሙስ መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታዉ ቡልቡላ ቦሎ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተዉ ጉድጓድ ዉስጥ ዕድሜዉ 33 ዓመት ሰዉ ህይወቱ አልፎአል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

በአዲስ አበባ ተቆፍረዉ ክፍቱን በተተዉና ዉሀ በአቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ ህይወታቸዉ የሚያልፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል።

እነዚህ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች የሚገኝባቸዉ ክፍለ ከተሞች እና የሚመለከታቸዉ አካላት መፍትሄ እንዲሰጡ ኮሚሽኑ አሳስቧል።
ከሶስት ቀን በፊት መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም በዚሁ ክፍለ-ከተማና ወረዳ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተወና ዉሀ በአቆረ ጉድጎድ ዉስጥ እድሜዉ 25 ዓመት የሆነ ወጣት ህይወቱ ማለፉ የሚታወስ ነዉ።

በተያያዘ ዜና
ዛሬ ሀሙስ መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ተሾመ ጫካ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ ዕድሜዉ 36 ዓመት የሆነ ሰዉ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል፡፡

የክረምቱ ጊዜ የአልተጠናቀቀ በመሆኑ ህብረተሰቡ ወንዝ አካባቢ የሚኖረዉን እንቅስቃሴ እንዲገደብና አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply