ተቋርጦ የቆየዉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የቫይረሱን ስርጭትን ከግምት ባስገባ መልኩ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገለፀ

ተቋርጦ የቆየዉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የቫይረሱን ስርጭትን ከግምት ባስገባ መልኩ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየዉ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።:
የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራምን አስመልክቶ አዲስ ለተቋቋመዉ አስፈፃሚ ግብረ ሀይል ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናዉን የከፈቱት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰላም ግንባታ ዳይሬክተር ጀነራል ወይዘሮ አስማ ረዲ የሰላም ሚኒስቴር በጎ ፈቃደኝነትን ለሰላምና ለብሔራዊ መግባባት ለማዋል ሰፊ ስራ እየሰራ ነዉ ብለዋል ።
”የወጣት በጎ ፈቃደኝነት ለነፃ አስተሳሰብ እና ሀገራዊ ብልፅግና ” በሚል መሪ ሃሳብ በመላዉ ሀገሪቱ የሚተገበረዉ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ስብዕና ግንባታ፣ ሀገራዊ አብሮነትን ማጠናከር፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጎልበትና ሰላም ግንባታ ላይ ትኩረት ያደርጋል ነው ያሉት ።
የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም በቅርቡ በመላዉ ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከግምት ባስገባ መልኩ ቅድመ-ዝግጅት በማድረግ ወደ ተግባር ይገባል።

The post ተቋርጦ የቆየዉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የቫይረሱን ስርጭትን ከግምት ባስገባ መልኩ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply