ተንቀሳቅሰን ለመስራት ተቸግረናል ሲል ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ አስታወቀ፡፡

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰን ለመስራትና ሰብዓዊ መብት አያያዞች ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት አስቸጋሪ አድርጎብናል መባሉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው ስብስብ ለሰብዓዊ መብት መብቶች በኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ መሠረት አሊ ግጭቶች ወዳሉበት አካባቢ ተንቀሳቅሰን የሰብዓዊ መብት ሁኔታዎችን መመልከት አልቻልንም ብለዋል፡፡

በሳለፍነው አዲስ ዓመት ከተለያዩ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ግጭቶች እንዲቆሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሯ አሁንም የታዩ የሰላም ድርድሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሲሉ ጥሪ አድርገዋል፡፡
በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ከዚህ ወደባሰ የሆነ ችግር ከመሸጋገሩ በፊት መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

መንግስት እንዲሁም ሌሎች በትጥቅ ትግል ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ወደ ድርድርና ሰላማዊ ውይይት እንዲመጣ ጥረት ማድረጋቸውን የሚናገሩት ወይዘሮ መሠረት ተጠያቂነትና እና ፍትህ እንደሰፍን ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ስኬታማ መሆን አልቻለም ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply