ተአምራዊው ባይካል ሀይቅ – ኢትዮጵያዊ ወንዞች

በዓለም ካሉት እንደ መለያ ድንበርም በማገልገል ላይ ከሚገኙ ትልቆቹ እና ጥልቅ ሀይቆች መካከል የቪክቶርያ ሀይቅ፣ የማላዊ ሀይቅ ወይም የታንጋኒጋ ሀይቅን የመሳሰሉ ይጠቀሳሉ አንዳንዶቹም በምሥራቅ አፍሪቃ ይገኛሉ።

እነዚሁ ሀይቆች በግዛት ይገባኛል ጥያቄ ወይም በተፈጥሮ ሀብት ቁጥጥር ለሚነሱ ውዝግቦች አዘውትረው ምክንያት ሲሆኑ ይታያል። ቅኝ ገዢዎች በመንግሥታት መካከል ያለውን ድንበር እንደፈለጉት አዘውትረውም  ሀይቆቹን ተከትሎ እንዲያልፍ አድርገው መከፋፈላቸውን ምሁራን ያስረዳሉ።

በዚህም የተነሳ ነው ዛሬም ለውዝግብ መነሻ ምክንያት የሆነው። አንዳንድ ሀገራት በግዛት ይገባኛል ጥያቄ ውዝግብ በሚነሳበት ጊዜ ይህንኑ የቅኝ አገዛዝ ዘመን ድንበር አሰማመርን በመጥቀስ ይከራከራሉ። ለምሳሌ ማላዊ የ1890 ዓም የተደረሰ ስምምነትን በመጥቀስ ባለቤትነቱ የታንዛንያ የሆነውን የማላዊ ሀይቅ ሰሜናዊ ክልል የሷ እንደሆነ ትከራከራለች።

በዚያን ጊዜ ጀርመን ሀይቁን በጠቅላላ ያኔ የብሪታንያ ግዛት ለነበረችው የዛሬዋ ማላዊ ትሰጣለች። ግን ሁለቱን ሀገራት የሚለየው ድንበር በሀይቁ ውሀ ውስጥ ስለሚያልፍ ውዝግብ ተፈጠረ። እርግጥ፣ ማላዊ ጉዳዩን ለዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንደምታቀርብ ብትዝትም፣ ይህን ዛቻ እስከዛሬ እውን አላደረገችም። በአፍሪካ ያሉ ሀይቆች በእንደዚህ አይነት ውዝግብ ውስጥ ቢሆኑም ሌሎች አገራት ሀይቆቻቸውን ለአለም ቱሪዝም መስህብነት አንዲውል እያደረጉ ነው ኢትዮጵያዊ ወንዞች ዝግጅታችንም ስለ አንድ ታላቅ ሀይቅ ታምራዊነት ያስቃኘናል!!!!!

ኣዘጋጅ፡ሊዲያ አበበ

ቀን 22/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply