
#ተከዜ ወንዝ! በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰሃላ ሰየምት ወረዳን ከሰቆጣ ጋር የሚያገናኜው የተከዜ የብረት ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ሪፈር የሚያስፈልጋቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ሕይወት እየጠፋ ነው ብለዋል። የተከዜ ድልድይ በመፍረሱ እናቶች ወደ ጎንደር እና ባህርዳር ሂደው እንዲታከሙ የሚያስገድዳቸው ቢሆንም፤ የተከዜ ወንዝን መሻገር እንደማይቻል ገልጸዋል። በሕክምና ዕጦት በሦስት ወራት ብቻ የሦስት እናቶች ሕይወት መጥፋቱንም ጨምረው ተናግረዋል። ድልድዩ በ2013 እንደተደረመሰ አሁንም ድረስ ከአገልግሎት ውጭ ሲሆን፤ እንደ አዲስ ለመስራት የድልድዩን ተሸካሚ መሰረት ለማቆም ቁፋሮ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም ድጋሚ የተከዜ ወንዝ ጠራርጎ እንደወሰደው ነው ነዋሪዎች የተናገሩት። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post