You are currently viewing “ተደራራቢ ጥፋት!” ደመወዝ ካሴ መኮንን _በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአብን ሰብሳቢ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ በትግሬ ወራሪ ምክ…

“ተደራራቢ ጥፋት!” ደመወዝ ካሴ መኮንን _በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአብን ሰብሳቢ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በትግሬ ወራሪ ምክ…

“ተደራራቢ ጥፋት!” ደመወዝ ካሴ መኮንን _በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአብን ሰብሳቢ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በትግሬ ወራሪ ምክንያት በህዝባችን ላይ ለደረሰው ሁለንተናዊ ውርደት መጠኑ ቢለያይም ሁላችን የወንጀል፣የሞራልና የታሪክ ተጠያቂነት አለብን። የጠላቶቻችን ሴራ እኔደተጠበቀ ሆኖ ፣ወራሪው ሀይል በወሎ፣ በጎንደርና በሸዋ ላደረሰው ጥፋት ሁሉም ልሂቅና ፓለቲከኛ በአጠቃላይና የየአካባቢው ልሂቅና ፓለቲከኛ በተለየ ሁኔታ ሀፍረት ሊሰማው ይገባል። ከዚህ በተቃራኒ በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰውን ውርደት በአውራጃ ከፋፍሎ “ተካድን” ብሎ ሌላኛውን አውራጃ ለመጥላትና የትህነግ ወይም የኦነግ በትር ለመሆን መፍጨርጨር አይን ያወጣ ስንፍናና ከሀዲነት ነው። የራሱን አካባቢ በተለይና የአማራን ህዝብ በአጠቃላይ አስተባብሮና አደራጅቶ ጠላትን መመከት ሲገባ የራስን ሀላፊነት ወደ ጎን በመተው ለደረሰው ጥፋት ሌላኛውን ወንድሙን ለመጥላት ሰበብ መፈለግ አይን ያወጣ ነውረኝነት ነው። ሁሉም አማራ የየራሱን አካባቢ መጠበቅ እንዳለ ሆኖ እንደ አንድ ህዝብ መተባበር አለበት። በዚህም ምክንያት የሁሉም አማራ ደምና አጥንት በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ ፈሷል፣ ተከስክሷል፣ ፣ ከፍተኛ ዋጋ ተከፍሏል። ከዚህ በተቃረነ ሁኔታ አንዳንዶች አማራነትን “በተግባር” አላየነም ይሉና እራሳቸው ግን እንኳን በተግባር በንግግርም አማራነትን ጠብ እርግፍ አድርገው ትተውታል። በእርግጥ አማራነትን “በተግባር” ማሳየት ዋናው አዋጭ መንገድ ነው፤ ዋናውን የአማራ ህዝብ ጥያቄ እረስቶ የአማራን ስም ለመጥራት መጠየፍ ግን ወራዳነት ነው፤ ለራስ ክብር አለመስጠት! ይልቁን ደግሞ አማራን በአውራጃ እየከፋፈሉ “ኢትዮጵያ ትባረክ” ይሉት አስመሳይነት በሌሎች ኢትዮጵያውን (የእውነት ካሉ) ትዝብት ውስጥ መግባትን እንጅ አንድም ጠብ የሚያረገው ነገር የለም፤ ኢትዮጵያን ለማትረፍ ከአማራ ህዝብ በላይ ሀጥያቷን ተሸክሞ ጀርባው የጎበጠ አንድም ኢትዮጵያዊ አይገኝምና! እንዲሁም ከራሳቸው ውጭ የመጡበትን አውራጃ 13 ሰዎች እንኳን መወከል የማይችሉ ሰነፎችና ጥቅመኞች የአውራጃው ተወከይ እንዳልሆኑ በግልፅ ሊነገራቸው ይገባል። የትግሬ ወራሪና የኦሮሙማ ዋጭ ሰልቃጭ የመሰሉ ጠላቶች ከፊታቸው አቁመው የራሳቸውን ወንድሞች የሚጠሉ ስልቦችን አደብ ማስገዛትና ከንቱ ጩኸታቸው እንዲሰል/እንዳይሰማ ማድረግ ይገባል፤ ከህዝባችን አንድነት በላይ የሆነ ነገር የለምና! ክፋት ከሌለብን በስተቀር ከሚለያየን ይልቅ ይበልጥ አንድ የሚያደርገን ነገር ስፍር ቁጥር የለውምና! ፖለቲካችን ከጫጫታ ወጥቶ በእውቀትና በሀሳብ ቢመራ መልካም ነበር። ይሁን እንጅ የእውቀትና የሀሳብ ፓለቲካ እስኪመጣ የአፍራሽነት ሚና ባለመጫዎት ከተቻለም የራስን መክሊት ለይቶ አወንታዊ አስተዋፅኦ ለማድረግ የራሳችንን ጠጠር መወርወር ይገባል። ፌስ ቡክ ላይ ተጎልቶ መሳደብ፣ ትዕዛዝ መስጠትና መንጫጫት ቁም ነገር ስላልሆነ ከዚህ ወጥተን መሬት ላይ ስራ እንስራ። ቢያንስ የህዝብ ሸክም ላለመሆን ለራሳችን ቃል መግባትና በተግባር መገለጥ ይገባል። በመጨረሻም በብአዴን ተስፋ ስለማላደርግ በመደሰትም ሆነ በመከፋት ጊዜዬን አላባክንም። በገነነው የተላላኪነት መንፈሱ የራሱን ወንድሞች ከሚበላ ቡድን ጋር ህብረት የለኝም። በራሳችን መንገድ ለመሄድ ልቦና ይስጠን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply