ተገቢ ያልሆነ የምርት ክምችት የሚፈጥሩ ነጋዴዎች የእስር ቅጣትን ጨምሮ እስከ 125ሺህ ብር ድረስ ይቀጣሉ ተባለ።ይህንን ያለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ነው።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድ…

ተገቢ ያልሆነ የምርት ክምችት የሚፈጥሩ ነጋዴዎች የእስር ቅጣትን ጨምሮ እስከ 125ሺህ ብር ድረስ ይቀጣሉ ተባለ።

ይህንን ያለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በክልሉ ያለአግባብ ምርት የሚያከማቹ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር አስተማሪ መመርያ ማውጣቱን አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት ተገቢ ያልሆነ የምርት ክምችት በማድረግ ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረት በሚፈጥሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ ለመውሰድ መመርያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ማንኛውም ነጋዴ ካስመዘገበው አጠቃላይ ካፒታል አንድ አራተኛ በላይ ዋጋ የሚያወጣ ምርት ከአንድ ወር በላይ ማከማቸት እንደማይችል ያስረዱት አቶ ዳንኤል ይህን በሚተላለፉ ላይ ንብረቱን ሙሉ በሙሉ የመውረስ እንደዚሁም ከ100 ሺህ እስከ 125ሺ ብር እና የእስር ቅጣት ተፈጻሚ ይሆናል ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው፣ ሳያሳድሱ፣ ከፈቃድ ውጭ ዘርፍ በመቀየር በሚንቀሳቀሱ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ከ150ሺ እስከ 300ሺ ብር ፣ከ7 እስከ 15 አመት የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልባቸውም ጠቁመዋል።

የዚህን ተፈጻሚነት በሚያስተጓጉሉ ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከ5ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልባቸውም ተናግረዋል።

ከዚሁ ጋርም ሀሰተኛ መረጃን በመጠቀም ንግድ ፈቃድ ለማውጣትና ሌሎችንም ህገ ወጥ ድርጊቶችን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ከ60 እስከ 120 ሺ ብር ወይም ከ7 እስከ 12 አመት እስራት እንደሚጠብቃቸው አስረድተዋል።

ሁሉም ህጋዊ የንግድ ድርጅት የሁሉንም የምርት አይነቶች ዋጋ ዝርዝር በሴክተሩ የተዋረድ መዋቅር ማህተም በማስደገፍ በግልጽ ቦታ ላይ የመለጠፍ ግዴታ እንዳለበትም አስረድተዋል።

ካልሆነ ህጋዊ ተጠያቂነት ይከተላል ሲሉም አክለዋል።
ባለፉት 6 ወራት በክልሉ 27ሺ የሚሆኑ ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ መስመር ማስገባት እንደተቻለም አስታውቀዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

የካቲት 04 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply