ተገድሎ የተገኘው ኬንያዊ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች መብት ተሟጋች ቀብር ተፈጸመ

https://gdb.voanews.com/022a0000-0aff-0242-9665-08daf00de1e4_w800_h450.jpg

ኬንያ ውስጥ ከሁለት ሳምንታት በፊት አስከሬኑ በብረት ሳጥን ውስጥ ተደርጎ ተጥሎ የተገኘው ታዋቂ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች መብት ተሟጋች ቀብሩ ትናንት ምዕራብ ኬንያ ውስጥ ተፈጽሟል።

በኤድዊን ቺሎባ ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በጓደኞቹ እና በመብት ቡድኖች የተወገዘ ሲሆን ፍትህ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

የሃያ አምስት ዓመቱ ሞዴል እና የፋሽን ዲዛይነር በማኅበራዊ መገናኛ ላይ ዛቻ ሲደርስበት የቆየ ሲሆን የኬንያ መንግሥት ዋናው የአስከሬን ምርመራ ኃላፊ ባለፈው ሳምንት በሰጡት ቃል ትንፋሹ እስኪቆረጥ ታፍኖ እንደተገደለ ገልጸዋል።

የሟቹ ፍቅረኛ የሆነው ፎቶግራፍ አንሺ በግድያው ተጠርጥሮ የተያዘ ሲሆን ሌሎች አራት ሰዎችም ተይዘዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply