ተጨማሪ 485 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 701 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 7 ሺህ 45 የላብራቶሪ ምርመራ 485 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡…

ተጨማሪ 485 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 701 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 7 ሺህ 45 የላብራቶሪ ምርመራ 485 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 93 ሺህ 343 ደርሷል።

ከዚህ በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰዓታት የ 7 ሰዎች ህይዎት በማለፉ በሀገራችን በቫይረሱ ሳቢያ ህይዎታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሺህ 426 ከፍ ማለቱን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ያደረሰን መረጃ ያስረዳል።

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት 701 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 47 ሺህ 543 መድረሱን የሚኒስቴሩ ዕለታዊ መግለጫ ያሳያል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply