ተጨማሪ 604 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 65 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 466 ሰዎች የላቦራቶሪ ተደርጎ 604 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 109 ሺህ 534 መድረሱንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በሌላ በኩል 1 ሺህ 65 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም 69 ሺህ 315 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት የአምስት ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ያለፈ ሲሆን እስካሁንም 1 ሺህ 700 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉንም አስታውቋል።

The post ተጨማሪ 604 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 65 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply