ተጨማሪ 841 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 588 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 997 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 841 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 230 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም 588 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 38 ሺህ 904 ደርሷል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት የ14 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 301 መድረሱን ገልጸዋል፡፡

እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 356 ሺህ 630 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 85 ሺህ 136 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ ቁጥር 38 ሺህ 904 ከቫይረሱ ሲያገግሙ 44 ሺህ 929 ሰዎች ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ አለባቸው ብለዋል፡፡

The post ተጨማሪ 841 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 588 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply