ተፈናቃይ በመምሰል በሽሬ ከተማ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጁንታው አመራር በቁጥጥር ስር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም           አዲስ አበባ ሸዋ በባዕከ…

ተፈናቃይ በመምሰል በሽሬ ከተማ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጁንታው አመራር በቁጥጥር ስር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በባዕከ…

ተፈናቃይ በመምሰል በሽሬ ከተማ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጁንታው አመራር በቁጥጥር ስር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በባዕከር፣ በሁመራና በቃፍታ አካባቢዎች የሚሊሻ ዋና አስተባባሪ በነበረበት ወቅት በንጹሃን ላይ ግፍ ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረ ግለሰብ በሽሬ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ። የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የብረት ለበስ አዛዥ ሻምበል አማኑኤል በለጠ፣ እንኳአየነው መሰለ የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለው ተፈናቃይ በመምሰል በሽሬ ከተማ ሲንቀሳቀስ ነው ብለዋል። ግለሰቡ በባዕከር፣ ሁመራና ቃፍቲያ አካባቢ የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊና የፀጥታ ዘርፍ አስተባባሪ በመሆን የጁንታው የጥፋት ተልዕኮ ሲያስፈጽም መቆየቱንም ነው የገለጹት። የህወሓት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አራት ቀናት ቀደም ብሎ “ሰራዊቱ በወለጋና በትግራይ ክልል ጭፍጨፋ እያካሄደ ነው” በሚል የሀሰት መረጃ በማሰራጨት የጥፋት ቅስቀሳ ሲያካሂድ እንደነበርም ተናግረዋል። የጁንታውን ሚሊሻዎች በማስተባበር መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም በማድረግ ረገድም ጉልህ ሚና እንደነበረውም ጠቁመዋል። በክፍለጦሩ የሁለተኛ ብርጌድ አባል ሃምሳ አለቃ ምህረት ደምሌ በበኩላቸው ተጠርጣሪው ከዚህ ቀደም ስልጣኑን በመጠቀም በተለይ አማራ ተወላጆች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጭቆና ሲፈፅም መቆየቱን ተናግረዋል። “የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ መለያን ለብሳችኋል እንዲሁም ‘የእገሌን’ ሙዚቃ አዳምጣችኋል” በሚል ምክንያት በንጹሃን ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈጸም የሚፈለግ ተጠርጣሪ መሆኑንም ነው የተናገሩት። በአካባቢው የተለያዩ የፍተሻ ጣቢያዎችን በማቋቋም የሀገር መከላከያ ሰራዊት መደበኛ እንቅስቃሴን ሲያስተጓጉል መቆየቱንም ጠቅሰዋል ሲል ኢትዮ መረጃ ኒውስ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply