ተፈናቃዮችን ማቋቋም የጦርነትን ያህል ይከብዳል – ፕ/ ሳኅለወርቅ

በጦርነት የተፈናቀሉ ሰዎችን መልሶ ሟቋቋም ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠው ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አሳሰቡ። 

ተፈናቃዮችን ወደየአካባቢያቸው መመለስ “የጦርነትን ያክል” ከባድ እንደሆነ የገለፁት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በማቋቋሙ ጥረት ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል። 

ድሬዳዋ ላይ ዛሬ በተከበረው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ “ስለ ሃገር መፍረስ የሚነሳው ሃሳብ ከሁሉም ሰው ኅሊና ሊጠፋ ይገባዋል” ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply