ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከኦዚ ሆስፒታሊቲና ቢዝነስ ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ


(ቱኢ)ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከኦዚ ሆስፒታሊቲና ቢዝነስ ግሩፕ ጋር ዛሬ በአያት ሪጄንሲ ሆቴል የሀገራችንን ቱሪዝም ለማስተዋወቅ እና በሆስፒታሊቲ ዘርፍ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማጠናከር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የገንዘብ ሚንስቴር፣ የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር፣ የቱሪዝም ኢትዮጵያ፣የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር፣የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ባሕልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማኅበር አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ የገንዘብ ሚንስቴር ዴኤታ እንደተናገሩት ሀገራችን በቱሪዝም ዘርፍ መጠቀም በሚገባት መጠን እንዳልተጠቀመች እና መንግስት ሕዝብ ከዘርፉ እንዲጠቀም ዘርፉን ለማሳደግ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ ስለሺ ግርማ የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር መንግስት የቱሪዝም ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያና የሀገር ዕድገት ያመጣልኛል ብሎ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በመዲናችን አዲስ አበባ የእንጦጦ፣የሸገር እና የአንድነት ፓርኮች በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ፕሮጄክት በጥራት ተገንብተው መጠናቀቃቸውን ጠቁመው ገበታ ለሸገር ፕሮግራም አልቆ ወደ ገበታ ለሀገር በመሸጋገር በወንጪ፣ በጎርጎራ እና በኮይሻ ከፍተኛ የቱሪዝም መዳረሻዎች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ቱሪዝም ኢትዮጵያ የማይስ ቱሪዝምን ለማሳደግ ከኦዚ ሆስፒታሊቲና ቢዝነስ ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ለዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ዋና ዳይ ሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
አቶ ቁም ነገር ተከተል የኦዚ ሆስፒታሊቲና ቢዝነስ ግሩፕ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረው ወደፊት ስኬታማ ስራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
Source:- Tourism Ethiopia

The post ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከኦዚ ሆስፒታሊቲና ቢዝነስ ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply