ቱርክ በሰሜን ሶሪያ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ልታካሂድ እንደምትችል ገለፀች

ቱርክ በሰሜን ሶሪያ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ልታካሂድ እንደምትችል ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቱርክ በሰሜን ሶሪያ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ልታካሂድ እንደምትችል አስጠንቅቃለች።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን እንደገለጹት፥ ኩርዲሽ የተሰኙት ታጣቂዎች ሀገሪቱ ከሶሪያ በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ አላስፈላጊ ትንኮሳ እያካሄዱ ነው።

ታጣቂዎች ከድርጊታቸው ተቆጥበው ስፍራውን ለቀው የማይወጡ ከሆነም አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ይካሄዳል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ።

ሰሞኑን ሩሲያ በኢድሊብ በሚንቀሳቀሱት እና በቱርክ በሚደገፉት የሶሪያ አማጺያን ላይ የወሰደችው የአየር ጥቃት ተቀባይነት እንደሌለውም አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም እርምጃው በቀጠናው ዛላቂ ሰላም ለማምጣት የተጀመረውን ሂደት የሚያደናቅፍ መሆኑን ነው የገለጹት።

ምንጭ፦ አናዶሉ

The post ቱርክ በሰሜን ሶሪያ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ልታካሂድ እንደምትችል ገለፀች appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply