ቱኒዚያ የአውሮፓ ፓርላማ ልዑክ ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

https://gdb.voanews.com/fd56a748-4f05-4b61-bc68-35077c380f52_w800_h450.jpg

ግራ ዘመም የአውሮፓ ፓርላማ ዓባላት ቱኒዚያ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በስደተኞች ጉዳይ ላይ ያደረገችውን ስምምነት መተቸታቸውን ተከትሎ፣ መንግሥት ወደ ሀገሪቱ ሊመጡ የነበሩ የፓርላማ ዓባላትን እንዳይገቡ አግዷል፡፡

የፓርላማው የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ አባላት በቱኒዚያ ያለውን የስደተኞች ሁኔታ ለመመልከትና እውነታውን ለመገንዘብ ወደዛች ሀገር ለማቅናት በዝግጅት ላይ ነበሩ።

የአውሮፓ ኅብረት እና ቱኒዚያ በሜዲትሬኒያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ የሚፈልሱትን ስደተኞች ለማስቆም ባለፈው ሐምሌ ስምምነት አድርገው ነበር። ብራስልስ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ዩሮ ለቱኒስ ቃል ገብታ ነበር።

ባለፈው ሳምንት በተደረገ የፓርላማ ክርክር፣ የግራ ዘመም አባላቱ፣ “ሕብረቱ ከፈላጭ ቆራጭና  እና ፍልሰተኞችን በማንገላታት ከሚወነጀል አገዛዝ ጋር ሥምምነት አድርጓል” ሲሉ ተችተው ነበር። 

ትችቱን ተከትሎ የፓርላማው ልዑክ ወደ ሀገሪቱ ሊያደርግ የነበርውን ጉዞ ቱኒዚያ አግዳለች፡፡ የቱኒዚያን ውሳኔ ተከትሎ የግራ ዘመም የፓርላማ አባላቱ ስምምነቱ እንዲታገድ ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply