ታሊባን የቱርክ ኃይሎች በአፍጋንስታን እንዲቆዩ እንደማይፈቅድ አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ ቱርክ ባሰራጨው ዘገባ የታሊባን አፈቀላጤ መናገራቸውን ጠቅሶ የታሊባን ኃይል አንድም የቱርክ ወታደር በአፍጋንስታን ምድር እንዲቆይ አያስፈልገም ነው ያለው፡፡

የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኃይሎች ከአፍጋኒስታን ሙሉ በሙሉ መውጣታቸውን ተከትሎ ቱርክ የጦር ኃይሏ በሃሚድ ካርዛይ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማስፈር ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወቃል፡፡

ይሁንና የቱርክን እቅድ በዚህ ወቅት የሀገረቱን ዘጠና በመቶ የተቆጣጠረው ታሊባን የማይታሰብ ነው ሲል ማጣጣሉን የዘገበው አህቫል ነው፡፡

ቀን 17/11/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply