ታላቁ ሩጫን ጨምሮ የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በስኬት እንዲጠናቀቁ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተለመደ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ

ታላቁ ሩጫን ጨምሮ የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በስኬት እንዲጠናቀቁ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተለመደ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጪው ዕሁድ በአዲስ አበባ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫን ጨምሮ የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በስኬት እንዲጠናቀቁ የከተማው ነዋሪዎች የተለመደ ድጋፉቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠይቋል፡፡
የገና በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር እና የፀጥታ አካላትን በመደገፍ ላበረከተው አስተዋፅኦ ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡
የገና በዓል በአዲስ አበባ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎበት የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ያስታወሰው ኮሚሽኑ የፀጥታ ሃይሉ ከሃይማኖት አባቶች እና ከከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሁም ከአስተዳደር አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ በዓሉ በሰላም ሊከበር መቻሉን ገልጿል፡፡
በመጪው ዕሁድ ደግሞ በአዲስ አበባ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫን ጨምሮ የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በስኬት እንዲጠናቀቁ የከተማው ነዋሪዎች የተለመደ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ማሳሰቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ታላቁ ሩጫን ጨምሮ የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በስኬት እንዲጠናቀቁ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተለመደ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply