You are currently viewing ታላቁ ዘመቻ – ዘመቻ ዘመነ ካሴ 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 በእለተ አድዋ በባህርዳር ከተማ በርካታ ሺዎች የሚሳተፉበት ዘመቻ ተጠርቷል። ዝምታህን ስበር፣ ድብታህን ወርውር፣ ለወንድምህ አለ…

ታላቁ ዘመቻ – ዘመቻ ዘመነ ካሴ 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 በእለተ አድዋ በባህርዳር ከተማ በርካታ ሺዎች የሚሳተፉበት ዘመቻ ተጠርቷል። ዝምታህን ስበር፣ ድብታህን ወርውር፣ ለወንድምህ አለ…

ታላቁ ዘመቻ – ዘመቻ ዘመነ ካሴ 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 በእለተ አድዋ በባህርዳር ከተማ በርካታ ሺዎች የሚሳተፉበት ዘመቻ ተጠርቷል። ዝምታህን ስበር፣ ድብታህን ወርውር፣ ለወንድምህ አለሁልህ በል። ዝመት ለዘመነ ካሴ! ዝመት ለወንድሞችህ። #ስለ_ሃሙሱ_ዘመቻ ሃሙስ (የአድዋ የድል ቀን) እጅግ በርካታ ሺዎች ሆነን አርበኛ ዘመነ ካሴንና አብረውት የታሰሩ ፋኖዎችን ባህርዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት እንጠይቀዋለን፤ ፍትህን የደፈጠጡ እግሮች እንዲነሱም ድምጻችንን ከፍ አድርገን እንጠይቃለን። ለዚህም 50ሺ ጠያቂዎች በአንድ ጀንበር እንዘምታለን። ከሞኝ ሰፈር ሞፈር መቆረጡ የሚያንገበግብህ የባህርዳር፣ የወረታ፣ የአዴት፣ የመራዊና ሌሎች ከተማ ነዋሪ ተከተለን። #ከሃሙስ_በፊት_ግን አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ ሌሎች በክልላችን በእስር ላይ ያሉ ፋኖዎች እንዲፈቱ ነገ ማክሰኞና እሮብ ለክልላችን ከፍተኛ አመራሮች በተመሳሳይ ሰዓት (ማታ 2:00) ተመሳሳይ የጹሑፍ መልዕክት ወደ ሞባይላቸው በመላክ ጥያቄ እናቀርባለን። በተመሳሳይ ደቂቃ፣ ተመሳሳይ መልዕክት በሺህ ፍትህ ፈላጊዎች ይላካል። ▪ማክሰኞ ለዶ/ር ይልቃል ከፋለና ለአቶ ደመቀ መኮንን ▪እሮብ ደግሞ ለዶ/ር ጌታቸው ጀምበር፣ ለአቶ ግርማ የሽጥላ፣ ለአቶ ስዮም መኮንን መልዕክቱና የአመራሮቹ ስልክ ለመልክ 10 ደቂቃ ሲቀር ለህዝብ ይፋ ይደረጋል። #SHARE አድርጉትና ሚሊዮኖች ጋር ይህ የዘመቻ ጥሪ ይድረስ፤ ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችም አግዙን፤ እንተጋገዝ። ጥያቄያችን በሙሉ ህግን ያከበረ ሰላማዊና እያደገ የሚሄድ ይሆናል። እነዚህ ጥያቄዎች ህዝባዊ ንቅናቄን መፍጠር ያለሙና የፍትህ ጥያቄዎች እስኪመለሱ ድረስ እያደጉ የሚቀጥሉ የሚቀጣጡ ይሆናል። ~~~~~~ ያ እንዳለ ሆኖ ግን ጥያቄያችን እንዳለ ሆኖ ከህዝብ ጎን እየቆማችሁ ላላችሁ የክልላችን አመራሮች በሙሉ ትልቅ አክብሮትና ምስጋና አለን፤ አሁንም ግን የህዝብን ጥያቄዎችን በአፋጣኝ መልሱ እንላለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply