You are currently viewing #ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሙከራ ሂደቱን አጠናቆ ኃይል ማመንጨት ጀመረ።  ባህርዳር:-የካቲት 13/ 2014 ዓ.ም                  አሻራ ሚዲያ የዕኛነት ተምሳል፣ የአንድነት ማስተሳሰሪ…

#ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሙከራ ሂደቱን አጠናቆ ኃይል ማመንጨት ጀመረ። ባህርዳር:-የካቲት 13/ 2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የዕኛነት ተምሳል፣ የአንድነት ማስተሳሰሪ…

#ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሙከራ ሂደቱን አጠናቆ ኃይል ማመንጨት ጀመረ። ባህርዳር:-የካቲት 13/ 2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የዕኛነት ተምሳል፣ የአንድነት ማስተሳሰሪያ ገመድ የሕብረ ብሔራዊ ካባ፣ የጋራ ታሪክ ዐሻራና ማህተም፣ ከግድብም በላይ የትውልድ ጎምቱ ሐውልት ነው – ዓባይ። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ የመጀመሪያውን ኃይል ማመንጨት ጀምሯል። የቅድመ ኃይል ማመንጫ (early generation unit) በፈረንሳዩ አልስቶን ፍራንስ ኩባንያ እየተገነባ ነው። በቀደሙ የይስሙላ የግንባታ ዓመታት በርካታ የሳይንስና ጥሬ እቃ ችግር የነበረበት ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በርካታ የማሻሻያ ሥራዎች ተሠርተውለት እነሆ ኃይል ማመንጨት ለመጀመር በቅቷል። የኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድም ሃሩር ከበረታባቸው የጉባ ተራሮች ግርጌ ተላቅ ጀብዱ ፈፅሟል። 6 ሺህ 696 ኪሎ ሜትር የሚዘረጋውና 2 ሺህ 700 ሜትር ኪዩብ በሰከንድ ይወነጨፋል የሚባልለት ዓባይ አሁን ላይ ግስጋሴውን ገታ አድርጎ ወደ ውስጥ በአትኩሮት እንዲያጤን ተደርጓል፤ በሀገር እጅ ለሀገር ልጅ እንዲኾንም ተደርጓል። ዓባይ እስካሁን ከሀገር ሃብትነት ይልቅ መወጊያና መጠቂያ ኾኖ ቆይቷል፤ ዛሬም ቢኾን ”ለምን?” ሲሉ ክንዳቸውን እንሰቅስቅ ያሉትም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ጉዳዩም የአውሮፓ ሕብረት የፀጥታው ምክር ቤትን ጭምር ለተደጋጋሚ ስብሰባ አስቀምጧል። በነ ግብፅ የቀኝ ግዛት ዘመን በእንግሊዝ አደራዳሪነት በተደረገ ስምምነት ወንዙን ለመከፋፈል ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በዚህም ግብፅ 66 በመቶ ድርሻ ሲኖራት 22 በመቶ ደግሞ የሱዳን ነው። ቀሪው 12 በመቶ የሚኾነው ደግሞ በትነት የሚያልቅ ሲኾን ኢትዮጵያም ዓባይ ወደ ካይሮ ምድር መሸጋገሪያው እንጂ አንድም ድርሻ እንደሌላት ስምምነቱ ያትታል። አሁን ያ ታሪክና ምዕራፍ ተቀልብሷል፤ ዓባይ ጉዞው ተገትቷል፣ በቤቱ ማደር ከጀመረም ዓመታትን አስቆጠረ፤ አሁንም በድል ብስራትነት ኃይል መስጠት ጀምሯል። አሁን በጉባ ሰማይ ስር ሌላ ብርቱ የታሪክ ምዕራፍ ጅማሮ ኾኗል። መጋቢት 24/2003 ዓ.ም የመሰረት ድንጋዩ የተቀመጠው ግድቡ የውኃ ማንደርደሪያ (spiral)፣ የሲቪል፣ ኤሌክትሮ ሜካኒካል፣ የብረታብረት ገጠማና የኃይል መቀበያና ማሰራጫ ጣቢያ ሥራዎቹ በ7 ተቋራጮች እየተከናወኑ ነው። 10 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ጥቅጥቅ የአርማታ ሙሌት የሚፈልገው ዋናው ግድብ በጥሩ ሂደት ላይ ይገኛል። 14 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የዓለት ሙሌት የሚፈጀው የኮርቻ ግድብ (sadle dam) ተጠናቋል። ይህም 50 ሜትር ቁመትና 5 ሺህ 200 ሜትር ርዝማኔ አለው። የግንባታ ሂደቱ ሲጠናቀቅ 246 ኪሎ ሜትር ወይንም ከአዲስ አበባ ሻሸመኔ የሚሆን ርዝመት ወደ ኋላ የሚዘረጋው ሐይቁ የወደፊት ትልቁ ተስፋው እንዳለ ኾኖ በአንደኛና ኹለተኛ ዙር የውኃ ሙሌቱም ላብ ያጠመቃቸውን የጉባ ተራሮች ጭምር አረስርሶ እስትንፋስ ለግሷል። ኹለተኛው የኃይል ማመንጫም በቅርቡ ይጠናቀቃል። ዓባይ ብርሃን መስጠት ጀመረ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply