You are currently viewing ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግብጽን እና ሱዳንን ለምን ያሰጋቸዋል? – BBC News አማርኛ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግብጽን እና ሱዳንን ለምን ያሰጋቸዋል? – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/8d40/live/00b94a40-512f-11ee-8fad-05c0aa38cb29.png

ኢትዮጵያ አራተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ሙሌትን አከናውኛለሁ ማለቷን ተከትሎ ግብጽ ከናይል ወንዝ የማገኘው የውሃ መጠን አቅርቦት ላይ አደጋ የጋረጠ ነው ስትል ከሳለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቀናት በፊት የታላቁ የህዳሴ ግድብ አራተኛ እና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
በግድቡ የውሃ ሙሌት እና ከግድቡ በሚለቀቀው የውሃ መጠን ላይ ህጋዊ እና አስገዳጅ ሶስትዮሽ ስምምነት ካልተፈረመ ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌቱን ማከናወን እንደሌለባትም ግብጽ ስትወተውት መቆየቷ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply