
ታላቅ ህዝባዊ እንቢተኝነት በመላው አማራ‼️ የአማራ ህዝብ በአደባባይ ስለመብቱ የሚጠይቅበት የማይቀርበት ታላቅ ህዝባዊ ስላማዊ ሰልፍ እሁድ መጋቢት 24/2015 ዓ.ም በመላው አማራ ይካሄዳል ። በመሆኑም አማራዎች ያለንበት ወቅታዊ ሁኔታ ፤የመንቀሳቀስ ፣የማምለክ ፣ተንቀሳቅሶ ሀብት ንብረት የማፍራት ፣በፈቀድነው የአገራችን ክፍል የመኖር መብታችን እንዲሁም በህይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብታችን በኦሮሞ ገዢ ቡድኖች በታገደበት ፣የህልውና አደጋ ላይ እንገኛለን ። እኛ አማራዎች የምንገኝበት ወቅታዊ ምዕራፍ የታወጀብንን የዘር ማፅዳት ፣ማጥፋት እና ሁሉን አቀፍ የዘር ጭፍጨፋ ለመመከት የምንነሳበት ፣የምንተባበርበት እና ተደራጅተን በህዝባዊ ትግል ይህንን አስከፊ አማራ ጠል ስርዓተ መንግስት የምናስወግድበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ። እኛ የአማራ ህዝቦች ታሪክ ያለን ፣ታሪክ የምንሰራ ኩሩ ህዝቦች ነው ።የቀደምት አባቶቻችን ኢትዮጵያ ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፤ሳላስብሽ ብቀር ምላሴ ከትናጋዬ ትጣበቅ ብለን የምንምልላት አገራችን ናት ።ነገር ግን አማራን የማታከብር ፣የምታሳድድ ፣በጅምላ የምትገድል እንዲሁም የምታፈናቅል ኢትዮጵያ አናውቅም ። እርፉን ጥሎ መሳሪያ አንጠልጥሎ በደምና አጥንቱ ባቆያት አገር በህዝባችን ላይ የምትቀልድ ፣የምትመፃደቅ እና ለደረሰብ እጅግ ዘግናኝ ግፍ የማትራራ ኢትዮጵያ አናውቃትም ። ሞታችን ሠርጋቸን ከሚመስለው ስርዓተ መንግስት መፍትሄ አንጠብቅም ።ህልውናችን በክንዳችን እናስከብራለን ። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል ። ህልውናችን በክንዳችን‼️ የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post