You are currently viewing ታላቅ ኣውሮፓ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ – ብራስልስ ቤልጀም

ታላቅ ኣውሮፓ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ – ብራስልስ ቤልጀም

የኢትዮጵያ ኮሚውኒቲ በቤልጂየም በተለያዩ የአውሮፓ አገራት ከሚገኙ ማህበራት ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ለማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጅቷል፡፡

ሰልፉ የሚካሄደው ፌብሩዋሪ 16 ከሰዓት በኋላ ከ13፡00 ሰዓት ጀምሮ በብራሰልስ ከተማ ሹማን አደባባይ ላይ ነው፡፡

ስለሰልፉ አላማና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ከዚህ በታች በአባሪነት ከተያያዘው የሰልፉ ማስታውቂያ ላይ የሚያገኙ መሆኑን በአክብሮት ለመግለጽ አንወዳለን፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ስፍራ በመገኘት የተለመደ ተሳትፎዎትን እንዲያደርጉ ኮሚውኒቲው በአክብሮት ይጠይቃል፡፡

የኢትዮጵያ ኮሚውኒቲ በቤልጂየም

Leave a Reply