
ታዋቂው የፊልም ተዋናይ ብሩስ ዊልስ ዲሜንሺያ የተባለ የጤና ችግር እንደገጠመው ቤተሰቦቹ ይፋ አደረጉ። ቤተሰቦቹ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት መግለጫ “በመጨረሻም ግልጽ የሆነ ምርመራ መኖሩ እፎይታ ሰጥቶናል” ብለዋል። ብሩስ ዊልስ ያጋጠመው ይህ ዲሜንሺያ የተባለው የጤና ችግር አይነት እንቅስቃሴን እና ሌሎች ተፈጥሯዊ ሂደቶችን መቆጣጠርን አዳጋች የሚያደርግ ነው።
Source: Link to the Post