ታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ )ለመንግስት ማሳሰቢያ ሰጠ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በተለያዪ የሀገ…

ታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ )ለመንግስት ማሳሰቢያ ሰጠ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በተለያዪ የሀገራችን ክፍሎች በተደጋጋሚ ጊዜ በዜጎች ላይ አላግባብ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ ባልተገባ መንገድ ተስፋፍተው መቀጠላቸውን ተያይዞ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በዋናነት መጠበቅ ያለበትና ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ለጉዳዩ አስፈላጊውን ትኩረት ሰጥቶ አግባብ ያለዉ መንግስታዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣና መሰል ጥቃቶች ዳግመኛ እንዳይፈፀሙ የሚጠበቅበትን የቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በጥብቅ ለማሳሰብ እወዳለሁ ሲል መልዕክት አስተላልፏል በዚህ አጋጣሚ በነዚህ ጥቃቆች ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲምር እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናት እንዲሆንላቸው ከልብ እመኛለሁም ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply