ታዲዎስ ታንቱ፣ ተመስገን ደሳለኝ እና አልዓዛር ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአዛዎንቱን ጋዜጠኛና የታሪ…

ታዲዎስ ታንቱ፣ ተመስገን ደሳለኝ እና አልዓዛር ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአዛዎንቱን ጋዜጠኛና የታሪክ ጸሐፊ ታዲዎስ ታንቱን እንዲሁም የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን በዋስትና ከእስር የመፈታት ብይንን ለመሻር ወይም ለማጽናት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለፊታችን ሀምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ረፋድ 3:00 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ታዴዎስ ታንቱ በ15 ሺህ ብር፣ ተመስገን ደሳለኝ ደግሞ በመቶ ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈተው በተመሰረተባቸው ክስ ላይ እንዲከራከሩ የእስር ፍርድ ቤቶች ወስነው ነበር። ሆኖም ዐቃቤ ሕግ ከእስር እንዳይፈቱ በመቃዎም ለፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቁን ተከትሎ ክርክር እየተደረገ ይገኛል። በሌላ በኩል፣ ጋዜጠኛ አልአዛር ተረፈ በአዲስ አበባ ላምበረት በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ባለፈውሐሙስ፣ ሀምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በሁለት የመንግሥት የስለላ ሰራተኞች ታፍኖ ታስሯል። ፍ/ቤት ቀርቦ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። የእስሩ መንስኤ፣ “የሲሪላንካን ተቃውሞ በፌስቡክ አጋርተሃል፣ ችግኝ በዜጎች ደም ላይ የሚተከል ነው፤ ቢተክሉትም ቤተ መንግሥት ገብተን እንነቅለዋለን” ብለሃል የሚል መሆኑን ባልደረባው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ይፋ አድጓል። አልአዛር ለምን እንደታሰረ ሲጠይቅ፣ “ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተችተኃል” የሚል ምላሽ እንደተሰጠውም ተነግሯል ሲል ባልደራስ አጋርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply