You are currently viewing ታዲዎስ ታንቱ በቀረበባቸው አምስት ክሶች በአንዱ ነጻ ሲባሉ አራት ክሶች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 18 ቀን 2015 ዓ/ም           አዲስ አበባ…

ታዲዎስ ታንቱ በቀረበባቸው አምስት ክሶች በአንዱ ነጻ ሲባሉ አራት ክሶች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ…

ታዲዎስ ታንቱ በቀረበባቸው አምስት ክሶች በአንዱ ነጻ ሲባሉ አራት ክሶች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ታዲዎስ ታንቱ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል በቀረበባቸው በአራት ክሶች እንዲከላከሉ ሲል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በሙሉ ድምጽ ብይን ሰጥቷል። በ5ኛው ክስ በሚመለከት ግን መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነጻ ናቸው ተብለዋል። ታዲዎስ ታንቱ በሰኔ 20 ቀን 2014 የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በዐቃቤ ሕግ በየደረጃው ተደራራቢ ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል። የቀረቡባቸው አምስቱ ክሶችም:_ 1) የዐቃቤ ሕግ አንደኛ ክስ እንደሚያመላክተው በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/(1)ሀና አንቀጽ 257 /ሀ ሥር የተደነገገውን ድንጋጌ በመተላለፍ ታዲዮስ ታንቱ በግንቦት 11 ቀን እና በመጋቢት 22 ቀን 2014 ራስ ሚዲያ በተባለ የዩቲዩቭ ቻናል “ባርነት ይብቃ! ተኝተን አንሞትም” በማለት የአማራ ተወላጆች የጦር መሳሪያ እንዲያነሱ በማነሳሳትና ህዝባዊ አመጽ በመቀስቀስ ክስ ተመስርቶባቸዋል በተጨማሪም ጥር 20 ቀን 2014 በሀሌታ ሚዲያ የዩቲዩቭ ቻናል ታዲዮስ ታንቱ የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ በማነሳሳት፣ የአማራ ልጅ ኹሉም ጦር መሳሪያ መታጠቅ እንዳለበት በመግለጽ አገዛዙን መስማት የለበትም በማለት ቅስቀሳ መደረጉን ዐቃቤ ሕግ ጠቅሷል። በየካቲት 22 ቀን 2014 በ251 ሚዲያ ቻናል ደግሞ፤ አማራ በሌላ ብሔር ላይ ባህልና ሐይማኖቱን ለመጫን የመጣ መስሎ እንዲታይና ተነጥሎ እንዲጠቃ በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸው ዐቃቤ ሕግ በክሱ አመላክቷል። 2) በ2ኛ ክስ በተመለከተ ደግሞ፤ የጥላቻ ንግግርንና ሀሰተኛ መረጃን ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁ 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7/4 በመተላለፍ ታዲዮስ ታንቱ፤ በታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ/ሰላም በተባለ የዩቱዩቭ ቻናል የትግራይ ህዝብ እንደ ከሀዲና የአለም ውሸታም እንደሆነ በማድረግ ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል ሲል ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል። በዚሁ ክስ ላይ በራስ የዩቲዩብ ቻናል ሚያዚያ 23 ቀን 2014 “በኦሮሞ ሚስት ለማግባት የሰው ብልት ቆርጠው ቂቤ ተቀብተው ነው የሚያመጡት ሰው ቢያጡ አውሬ ገለው ያመጣሉ” በማለት በኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እንዲሁም፤ በገዳ ሥርዓት ከራሳቸው ጎሳ ውጪ ያለ ማንንም መግደል መብት እንደሆነ በመግለጽ የኦሮሞ ባህልን በማጉደፍ ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ ነበር ሲል በክሱ ዘርዝሯል። 3) በ3ኛ ክስ ደግሞ፤ የወንጀል ህግ ከአንቀጽ 32 /1ሀ ና አንቀጽ 337 በመተላለፍ የመከላከያ ሰራዊትን እቅስቃሴን ለማሰናከልና የመከላከል አደጋ እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ ሀሰተኛ ወሬ በመንዛት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር ሲል ዐቃቤ ሕግ ጠቅሶ በክሱ አስታውቋል 4) በ4ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁ 958/2008 አንቀጽ 14 በመተላለፍ ህዝባዊ አመጽ እንዲፈጠር ቀስቃሽ መልዕክት በድምጽና በተቀሳቃሽ ምስል ማሰራጨታቸው ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሯል። 5) በ5ኛ ክስ ላይ ደግሞ፤ የወንጀል ህግ አንቀጽ 244/1 በመተላለፍ በመጋቢት 29 ቀን በራስ የዩቲዩቭ ቻናል መንግስት ፀረ ኢትዮጵያ እንደሆነ አድርጎ በመወንጀልና መንግስትን በመሳደብ እና የማዋረድ ተግባር ፈጽመዋል ብሎ ዐቃቤ ህግ በታዲዮስ ታንቱ ላይ ክስ አቀርቦ እንደነበር ይታወቃል። እንደአጠቃላይ ፍርድ ቤቱ ከቀረበው ክስ ጋር የዐቃቤ ሕግ የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃን መርምሮ በዛሬው ቀጠሮ በቀረበባቸው በአራት ክሶች እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን የሰጠ ሲሆን፤ በ5ኛው ክስ ግን መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነጻ ናቸው ስለማለቱ የጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘገባ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply