ታጋይ ቀለብ ስዩም ላጋጠማት የጤና መታወክ ተገቢ ህክምና ያለማግኘቷ ጉዳይ እንዳሳሰበው የገለፀው ባልደራስ ከህክምና እጦት ጋር በተያያዘ አንዳች ችግር ቢፈጠር ማ/ቤቱ ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወ…

ታጋይ ቀለብ ስዩም ላጋጠማት የጤና መታወክ ተገቢ ህክምና ያለማግኘቷ ጉዳይ እንዳሳሰበው የገለፀው ባልደራስ ከህክምና እጦት ጋር በተያያዘ አንዳች ችግር ቢፈጠር ማ/ቤቱ ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አስጠነቀቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ታጋይ ቀለብ/አስቴር ስዩም ላጋጠማት የጤና መታወክ ተገቢ ህክምና ያለማግኘቷ ጉዳይ እንዳሳሰበው የገለፀው ባልደራስ ከህክምና እጦት ጋር በተያያዘ አንዳች ችግር ቢፈጠር ተቋሙ ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ለቃሊቲ ማ/ቤትና ለተለያዩ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በእስር ላይ ያሉ የድርጅቱ አመራር ቀለብ/አስቴር ስዩም ከጀርባ ህመም ጋር በተያያዘ ላጋጠማት የጤና መታወክ ተገቢ ህክምና እንድታገኝ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወቃል። ድርጅቱ ለቃሊቲ ማ/ቤት ትናንት ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም ላጋጠማት ህመም በህገ መንግስቱ መሰረት መብቷ ሳይሸራረፍ ተገቢ የህክምና እርዳታ እንድታገኝ የማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጡ ጠይቋል። በጀርባ ህመም እየተሰቃዬች የምትገኘው ቀለብ ስዩም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ አንዳች አደጋ ቢደርስ ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። በመሆኑም ቀለብ ስዩም በግሏ በመረጠችው የህክምና ማዕከል የመታከም መብቷ እንዲጠበቅላት አሳስቧል። ባልደራስ ደብዳቤን በግልባጭ ለፌደራል አቃቢ ህግ ጽ/ቤት፣ ለፌደራል ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት፣ለጤና ጥበቃ ጽ/ቤት፣ ለጤና ሚኒስትር፣ ለኢሰመኮ፣ለኢሰመጉ እና ለከፍተኛ ፍ/ቤት ይድረስ ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply