You are currently viewing ታጋይ አሸናፊ አካሉ፣ የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ፍትህአለው አሰፋ እና የአርበኛ ዘመነ ካሴ ሾፌር ፋኖ ዘሪሁን ለሶስቱም የዋስትና በድምሩ 43 ሽህ ብር ከተከፈለ በኋላ ከግፍ እስር ተፈ…

ታጋይ አሸናፊ አካሉ፣ የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ፍትህአለው አሰፋ እና የአርበኛ ዘመነ ካሴ ሾፌር ፋኖ ዘሪሁን ለሶስቱም የዋስትና በድምሩ 43 ሽህ ብር ከተከፈለ በኋላ ከግፍ እስር ተፈ…

ታጋይ አሸናፊ አካሉ፣ የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ፍትህአለው አሰፋ እና የአርበኛ ዘመነ ካሴ ሾፌር ፋኖ ዘሪሁን ለሶስቱም የዋስትና በድምሩ 43 ሽህ ብር ከተከፈለ በኋላ ከግፍ እስር ተፈተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ታጋይ አሸናፊ አካሉ፣የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ፍትህአለው አሰፋ እና የአርበኛ ዘመነ ካሴ ሾፌር ፋኖ ዘሪሁን የዋስትና ለሶስቱም በድምሩ 43 ሽህ ብር ከተከፈለ በኋላ የካቲት 24/2015 ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ከሰባታሚት የግፍ እስር መፈታታቸውን ከቤተሰብ የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በባህር ዳር እና አካባቢው ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት እነ ታጋይ አሸናፊ አካሉ የካቲት 21/2015 የዋስትና መብት የተፈቀደላቸው እና የተከፈለ ቢሆንም ማ/ቤቱ ማብራሪያ እፈልጋለሁ ማለቱን ተከትሎ ነው እስከ ዛሬ በእስር ላይ የቆዩት። የዋስትና ገንዘቡም:_ 1) አሸናፊ አካሉ 18 ሽህ ብር፣ 2) ዘሪሁን 15 ሽህ ብር፣ 3) ፍትህአለው አሰፋ 10 ሽህ ብር ነው። አሸናፊ አካሉ ለአንድ ሳምንት ገደማ ፍ/ቤት ሳይቀርብ በክልሉ የጸጥታ አካላት ለቤተሰብ አድራሻው ሳይገለጽ ታፍኖ መቆዬቱ ይታወሳል። በተመሳሳይ ፍትህአለው አሰፋም ለአንድ ሳምንት ገደማ አፈና ተፈጽሞበት ከቆዬ በኋላ ነው አድራሻው ታውቆ ወደ ፍ/ቤት የቀረበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply