
ታግተው ደብዛቸው የጠፉ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጉዳይ መነሻ ያደረገ “ህዳር 25” የተሰኘ የሲቪክ ማህበር ተመስርቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የታገቱ 17 የአማራ ተማሪዎችን መነሻ ያደረገ ነው የተባለ ማህበር መመስረቱ ተገልጧል። በአጠቃላይ ሴቶች እና ህፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል የተባለው “ህዳር 25” የተሰኘ የሲቪክ ማህበር ተመስርቷል። ይህ ማህበር የምስረታ ትውውቁንም የካቲት 22/2015 ከቀኑ 5:30 በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ያካሂዳል ተብሏል። የሚዲያ አካላት እና ፍላጎቱ ያላችሁ ሁሉ እንድትገኙልን የሚል የአክብሮት ጥሪም ቀርቧል። የዘገባ ምንጭ_ሮሃ ሚዲያ ነው።
Source: Link to the Post