ታጣቂዎች አማሮ ውስጥ ሦስት ሰው ገደሉ

https://gdb.voanews.com/A2494144-9A43-4CD4-A20B-30F8868F17EA_cx2_cy13_cw96_w800_h450.jpg

ታጣቂዎች በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ዳኖ ቀበሌ አደረሱ በተባለ ጥቃት ሦስት አርሶ አደሮች መገደላቸውን የቀበሌው ነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ቁጥራቸው ያልተገለፀ ከብቶቻቸው መዝረፋቸውንም ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በግድያውና በዘረፋው የከሰሱት ሸኔ ያሉትንና የኦሮሞ ነፃነት ጦር መሆኑን የሚናገረውን ታጣቂ ቡድን ሲሆን የቡድኑ ቃል አቀባይ ማምሻውን በስልክ በሰጡን ምላሽ አስተባብለዋል።

የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ አየለ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ሦስቱ አርሶ አደሮች መገደላቸውን አረጋግጠው ሁለት መቁሰላቸውን፤ የ12 አባወራዎች ከብት መዘረፉን ገልፀዋል።

ሙሉውን ከተያያዘው ዘገባ ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply