ታጣቂ ቡድኖች በደቡብ ምዕራብ ክልል ህዝበ ውሳኔ ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ተናግረዋልበቤንች ሸኮ ዞን በተለያዩ…

ታጣቂ ቡድኖች በደቡብ ምዕራብ ክልል ህዝበ ውሳኔ ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ተናግረዋል

በቤንች ሸኮ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የመሸገው ታጣቂ ቡድን በደቡብ ምዕራብ ክልል ህዝበ ውሳኔ ላይ አሉታዊ ተጽኖ ሊያሳድር ይችላል ተብሏል፡፡

በአካባቢው በተለያዩ ወረዳዎች መሽገው የሚገኙት ታጣቂ ቡድኖች ህዝበ ውሳኔው በሰላማዊ መንገድ እንዳይካሄድ ስጋት እየፈጠሩ ነው በማለት የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ተናግረልዋል፡፡

በዞኖቹ የመከላከያ እና የፌደራል የጸጥታ ሀይሎች በጋራ እየሰሩ ቢገኙም ካለው ስጋት አንጻር ያለው የጸጥታ ሀይል በቂ ባለመሆኑ የፌደራል መንግስት እና የክልል መንግስት ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኙት አምስት ዞኖች ራሳቸውን ችለው ክልል ለመሆን በየምክር ቤቶቻቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ምዕራባዊ ክፍል የሚገኙት የካፋ፣ የዳውሮ፣ የቤንች ሸኮ፣ የሸካ፣ የምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና የኮንታ ልዩ ወረዳ ከስምምነት ላይ የደረሱት በየምክር ቤቶቻቸው ባሳለፉት ውሳኔ መሰረት ነበር፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ህዝበ ውሳኔውን ለማከናወን ቀነ ቀጠሮ መያዙ ይታወቃል፡፡

ለህዝበ ውሳኔውም አምስቱም ዞኖች በክልል ደረጃ ለመደራጀት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ህዝበ ውሳኔም ሰላማዊ ሆኖ እንዲካሄድ ሚሊሻዎችን እያሰለጠኑ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply