ቴክኖ ሞባይል አዲሱን እና ዘመናዊ የስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ እና ስፓርክ ሲሪስ የሞባይል ሞዴል በኢትዮጵያ አስተዋዉቋል።

ስልኮቹ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ከፍተኛ የካሜራ ጥራትና የፕሮሰሰር አቅም፣ ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል ባትሪ፣ ማራኪ ቅርጽ እና ውበት የተላበሱ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በስፖርቱ አለም ተውዳጅ ከሚባሉት ዝግጅቶች አንዱ የሆነውን የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ይፋዊ ስፖንሰር መሆኑን የገለጸው ቴክኖ ሞባይል ይህን አዲሱን የሞባይል ሞዴል ከዚሁ የአህጉራዊ ስፖርት መረሀግብር ጋር በማስተሳሰር ቴክኖሎጂ እና ስፖርቱ ያጣመረ የማስተዋወቅ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችን በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እያከናወነ እንደሚገኝም አመልክቷል።

አዲሱ ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ ሞዴል በ108 ሜጋ ፒክስል አልትራ ሴንሴቲቭ (ultra-sensitive) የካሜራ ጥራት የተገጠመለት ሲሆን በ ኤ.አይ (AI) ሲስተም በመታገዝ በየትኛውም አይነት የብርሀን መጠን በምሽት ሆነ በቀን ጥርት ያሉ ፎቶዎችን ማንሳት ያስችላል ተብሏል።

በከፍተኛ ፍጥነት የተለያዩ መተግበሪያዎችን ያለእንክን እንዲያስተናግድ የሚያስችለው (G99 ultra boost) የተሰኘ ፕሮሰሰር ያለው መሆኑ እና 6.78 ኢንች አሞሌድ ስክሪን በ120Hz ሪፍሬሽ ሬት የሆነው ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ ተጠቃሚዎች ያለምንም እንከን በቅልጥፍና አንዲያገለግል ያደርገዋል፣ የሞዴሉንም የመያዝ አቅሙን በመጨመር 256 ጂቢ ሚሞሪ በ16 ጂቢ ራም ጋር የቀረበ ሲሆን 5000 mAh አቅም ያለው ባትሪ ከ33W ሱፐር ቻርጅንግ ሲስተም ያለው ሲሆን በአጭር ጊዜ 100% ባትሪ ቻርጅ ማድረግ አቅም ያለው የስልክ ሞዴል መሆኑ ተነግሯል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply