ቴክኖ ሞባይል አዲሱን ካሞን 20 የስልክ ሞዴል አስተዋወቀ፡፡የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ ሞባይል የአለም አቀፍ ሽ…

ቴክኖ ሞባይል አዲሱን ካሞን 20 የስልክ ሞዴል አስተዋወቀ፡፡

የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ ሞባይል የአለም አቀፍ ሽልማት የተጎናፀፈበትን ካሞን 20 የስልክ ሞዴል አስተዋዉቋል፡፡

የተለያዩ የስልክ ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች ሲያቀርብ የቆየው ቴክኖ ሞባይል ቴክኖሎጂን እና ዲዛይንን በማጣመር ተሰርቷል ያለዉን አዲሱን ካሞን 20 ሞዴል ስልክ በትናንትናዉ ዕለት የኩባንያው ሀላፊዎች አና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በታደሙበት ይፋ አድርጓል፡፡

ካሞን 20 ካሜራፎቶ እና ቪዲዮ እንቅስቃሴ ሳይረብሸው ማንሳት የሚያስችል በኤስ.ኤል,አር (SLR) ሲስተም የሚታገዝ ባለ ሁለት ሌንስ ካሜራ፣ በምሽት ጥራት ያለው 50 ሜጋ ፒክስል ምስል ለማንሳት የሚያስችለው አርጂቢደብሊው (RGBW) ሴንሰር የተገጠመለት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቴክኖ ካሞን 20፣ ካሞን 20 ፕሮ 5፣ ካሞን ፕሮ 5ጂ ካሞን ፕሪሚየር 5ጂ በሚባሉ አይነቶች ቴክኖ ሞባይልን በአለም ዙሪያ እያስተዋወቀ እንደሚገኝም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በዝግጅቱ ላይ የቴክኖ ሞባይል ብራንድ ማኔጀር ኤሊክ በመክፈቻ ንግግራቸው አዲሱ የካሞን 20 ሞዴላችንን ከምናስተዋውቅባቸው ሀገራት አንድዋ ኢትዮጵያ በመሆኗ ደስተኛ ነን ብለዋል፡፡

ይህ ለቴክኖ ሞባይል እና በአጠቃላይ ለአፍሪካ የሞባይል ኢንዱስትሪ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው ያሉት ኤሊክ ፣ካሞን 20 የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ለማሟላት የሚሰራውን ስራ በተመለከተ ወደፊት ከተጠቃሚዎች ዘንድ የሚመጣውን ምላሽ ለመስማትም ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

አዲሱን ካሞን 20 ሞዴል የማስተዋወቅ አካል የሆነው እና ቴክኖሎጂን እና ፋሽንን በጥምረት ያሳየ የፋሽን ሾው የተካሄደ ሲሆን፣ በምርቃት ፕሮግራሙ ላይም በሀገር ውስጥ እና በውጪ ታዋቂ የሆኑ የፋሽን ዲዛይነሮች የተዘጋጁ ዲዛይኖች የቀረቡበት ዝግጅትም ተካሂዶ ነበር፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply