ቴክኖ አዲሱን እና በቅርቡ በባርሴሎናው አመታዊ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ ያደረገውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በይፋ በኢትዮጲያ አስተዋወቀ።አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ…

ቴክኖ አዲሱን እና በቅርቡ በባርሴሎናው አመታዊ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ ያደረገውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በይፋ በኢትዮጲያ አስተዋወቀ።

አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው።

ቴክኖ በቅርቡ በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው አመታዊው የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን (Mobile World Congress) ላይ ይህን አዲስ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴልን ጨምሮ የተለያዩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በይፋ እንዳስተዋቀ የሚታወቅ ነው፣ በዚሁ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ የሆነው ቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በማንኛውም አይነት ሁኔታ እና የብርሃን መጠን ሳይገድበው ቁልጭ ያሉ ፎቶዎችን የማንሳት አቅም እንዲኖረው በማሰብ በካሜራ ቴክኖሎጂ ሶኒ (SONY) ምርት የሆነውን ዘመናዊ ሴንሰር (Sony IMX890) የተገጠመለት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ተብሏል።

በኢንዱስትሪው የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ‘PolarAce’ ፖላርኤስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የቪድዮ ኢሜጂንግ ሲስተሙን በማዳበር እና እንከን የለሽ በማድረግ የካሜራ ቴክኖሎጂውን ሁለቱ ኩባንያዎች ወደ ላቀ ደረጃ አድርሰውታል።

ከዚህም በተጨማሪ ፍጥነት እና እንከን የለሽ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያደርገው የፕሮሰሰር አቅም፣ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እየሰጠ መቆየት የሚችል ባትሪ፣ ማራኪ ቅርጽ እና ውበት ያለው የመጨረሻው የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ የሞባይል ስልክ ግብዓቶችን አካቶ የያዘ ነው።

የቴክኖ ሞባይል ኢትዮጲያ ብራንድ ማናጀር የሆኑት ሚስተር አሌክ ሁዋንግ  “አዲሱ ስልክ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከኤ. አይ ሲስተም ጋር በማስተሳሰር አዳዲስ ፈጠራዎችን ያቀረበ ሲሆን ይህም ቴክኖ እንደ ብራንድ በኢንደስትሪው ግባርቀደም ለመሆን እየሰራ ለመሆኑ ማሳያ ነው’’ ብለዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሰኢድ አራጋው በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ‘’ ኢትዮ ቴሌኮም እና ቴክኖ ሞባይል በጋራ በመሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ይሰራሉ’’ ያሉ ሲሆን ’’ የ4G እና 5G ስማርትፎን በሀገራችን ለማቅረብ እና ተደራሽ ማድረግ ግባችን ነው ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply