'ትህነግ በ አማራው ህዝብ ርዳታ በ 1983 ወደ ስልጣን ከመጣች ጀምሮ የ አማራው ህዝብ ሰቆቃ እና ዋይታ ተጠናክሮ ቀጥሏል' ከ አማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ የቀረበ ጥሪ ታህሳስ 10 ቀን…

‘ትህነግ በ አማራው ህዝብ ርዳታ በ 1983 ወደ ስልጣን ከመጣች ጀምሮ የ አማራው ህዝብ ሰቆቃ እና ዋይታ ተጠናክሮ ቀጥሏል’ ከ አማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ የቀረበ ጥሪ ታህሳስ 10 ቀን 20013 ዓ.ም ትህነግ በ አማራው ህዝብ ርዳታ በ 1983 ወደ ስልጣን ከመጣች ጀምሮ የ አማራው ህዝብ ሰቆቃ እና ዋይታ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከሽግግር መንግስቱ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተወካይ የሌለው እና ተቆርቋሪ አልባው አማራ ከ ቡኖ በደኖ፣ ጉራፈረዳ፣ አሰቦ፣አርሲ እስከ መተከል እና ወለጋ ድረስ የሚደርስለት አካል በመጥፋቱ እጅግ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል እየተፈጸመበትም ይገኛል። ሃገሪቷን እያስተዳደረ ያለው አካል ይህን የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸሙ ያሉትን ኦነግ እና ትህነግ ባሸባሪነት ይፈረጁ ተብሎ ለተነሳለት ጥያቄ ሲልመጠመጥ እና ሲንቀጠቀጥ እያስተዋልን ነው። ከ 30 ጊዜ በላይ ልዩ ሃይል አስልጥኜ አስመርቄያለሁ ያለው የ ኦሮሚያ ክልል በክልሉ የሚፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን መከላከል አልቻለም። ስለሆነም በማንነታችን ብቻ እየተለየን ለሚደርስብን የዘር ማጥፋት ወንጀል ኦነግ ሽኔ እና ኦሮሚያን እያስተዳደረ ያለው የክልሉ መንግስት ቀጥተኛ ተሳታፊዎች እና ተጠያቂ ናቸው ለማለት ያስደፍራል። በመተከል ላይ እየተፈጸመብን ያለው ግፍ የ በቤንሻንጉል ክልላዊ መንግስትት እየታገዘ የሚደረገው በደል ከምን ጊዜውም በላይ አሰቃቂ ሆኗል ሰው ገሎ ስጋውን እየበላ ያለን አካል በየትኛው ስነ አመክንዮ ሰው ነው ብሎ የሰው መብት ለመስጠት እንደታሰበ ግራ ያጋባል። ሰውን አድኖ ገሎ የሚበላ ከሰብዕ ውጪ የሆነ አውሬ በመሆኑ ይህ አውሬ ብዙ ፍጅት እየፈጸመ ስለሆነ ሰዋዊ ባህሪ የሌለው አውሬ በጊዜው መፍተሄ ሊሰጠው ይገባል። ለዚህም መላው የ አማራ ህዝብ ተደራጅቶ ከመጣበት አደጋ በራሱ ሊከላከል ግድ የሚልበት ጊዜ በመሆኑ መላው የ አማራ ህዝብ ከፈጣሪው በታች በነፍጡ እና በክንዱ ህልውናውን ማስከበር ይኖርበታል። አማራው ሃገር ሰርቶ ሃገር ገንብቶ ደም እና አጥንቱን ብሎም ውድ ህይወቱን ሰውቶ ባቆያት ሃገር ላይ ስለ ሃገር ፍቅር ምንም በማያውቁ ፣ ስለ ሃገር ሲባል የተከፈለው መሰዋዕትነት በማይገባቸው፣ምላሳቸው ሌላ ልባቸው ሌላ በሆኑ፣ የ እናት ጡት ነካሽ ታሪካዊ የ ሃገር ጠላት በሆኑ አካላት ትብብር እንደባይተዋር ተቆጥሮ በ ያለበት መገደል እና መሞት ብሎም መፈናቀል ሊበቃው ይገባል። ከዚህ በኋላ በአማራው ጥላቻ ላይ የተመሰረተው ፌደራሊዝም የሚያቀነቅነው ህገ መንግስት አማራውን የሚወክል ባለመሆኑ እና የአማራውን ውድ ህይወት እያጠፋ የሚገኝ አማራ ጠል ስርዓት በመሁኑ፣ አማራው ልዩ ሃይሉን ወይ ሚሊሻውን ችግሮች በተፈጠሩባቸው አካባቢዎች አስገብቶ ራሱን እንዳይከላከል ክልል በሚል መከፋፈያ ህግ ተሰርቶ መግባት አይቻልም በሚል ተልካሻ ምክንያት የ አማራው ልጆች እያለቁ ይገኛሉ። ሁሉም አማራ ከፈጣሪው እና ከ ራሱ በቀር መብቴን ያስከብርልኛል፣ ህይወቴን ይታደግልኛል የሚለው ምንም አይነት አካልም ሆነ መንግስት እንደሌለ ተገንዝቦ ህልውናውን በታሪክ ሂደት ውስጥ አቆይቶ በማስቀጠል ቅድመ ሁኔታ ላይ ጠላቶቹን ተደራጅቶ መመከት ስለሚገባው ሁላችንም ይህን የ አማራው የምጥ እና የሲቃይ ዘመን ተደጋግፈን እንድናልፍ ስንል በ ጭቁኑ አማራ ህዝብ ስም እንጠይቃለን። ወጣት ማህበራት፣ ፋኖ፣ የ አማራ ባለሃብቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያ አንቂወች፣ ዲያስፖራዎች ፣ ጋዜጠኞች ብሎም ያልተጠቀሳችሁ የ አማራው ሰቆቃ ይመለከተኛል የምትሉ አካላት ሁሉ በ ማንነታችን የሚደርስብንን ሰቆቃ ተባብረን፣ ተደራጅተን፣ አንዳችን ላንዳችን ቆመን እና ተደጋግፈን የምንመክትበት ጊዜ በመሆኑ ኑ አብረን እንታገል ይላል የ አማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ። የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 10 2013 አ/ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply