ትህነግ እና ኦነግ ሽኔ በአሸባሪነት እንዲጠየቁ ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣ…

ትህነግ እና ኦነግ ሽኔ በአሸባሪነት እንዲጠየቁ ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣ…

ትህነግ እና ኦነግ ሽኔ በአሸባሪነት እንዲጠየቁ ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ያስተላለፈው መልዕክት የሚከተለው ነው:_ ትህነግ እና ኦነግ ሽኔ በአሸባሪነት ስለመጠየቅ! እንደተሞከረው በእርሶ የስልጣን ዘመን ለመናገርም ሆነ ለመስማት የሚዘገንን በአማራው ማህበረሰብ ላይ ዘርን ምክንያት ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲካሔድ ቆይቷል። አሁንም በተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየተካሄደ ነው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ተጠያቂ ሁለቱ የሃገራችን ነቅርሳዎች ማለትም ትህነግ እና ኦነግ ሽኔ ናቸው። ይሁን እና እነዚህን አካላት በ አሸባሪነት ለመፈረጅ ሲያቅማሙ እያስተዋልን እንገኛለን ለዚህም ምስክራችን ትላንት በፓርላማ በ አሸባሪነት ይፈረጁ ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ በቂ መልስ አለመስጠትዎ ነው። ጭራሽ በሚሊዮኖች ተፈናቅለው መልሰን አቋቁመናል ልምድ አለን የ አሁኑ ትንሽ ነው እንወጣዋለን። ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት ከመከላከል ይልቅ ከተፈጠሩ በኋላ የማስተካከል ፍላጎት ያለ የሚመስል አንደምታ ያለው ንግግር አድርገዋል። ስለሆነም የ አማራ ወጣቶች በሸዋ በ ትህነግ እና በ ኦነግ ሽኔ ምክንያት ዛርን መሰረት ያደረገ ጥቃት በማድረሳቸው እና እንዲደርስ በማስተባበራቸው ሃገሪቷ ለአማራው ማህበረሰብ ትልቅ የስጋት ቀጣና ሆናለች ብሎ ያምናል። ስለዚህ እነዚህ ሁለት አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአሸባሪነት ተፈርጀው ህግ የማስከበሩ ስራ እንዲጀመር እና ዜጎች በማንነታቸው ብቻ የሚደርስባቸው በደል እንዲቆም ስንል እንጠይቃለን። የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ

Source: Link to the Post

Leave a Reply